ፍትህ ሚኒስቴር ሊፈርስ ነው አሉ….. (አቤ ቶኪቻው)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ፍትህ ሚኒስቴር ሊፈርስ ነው አሉ….. ‘’የባልሽ ቂጣ እንክትክቱ ይውጣ….’’ ብዬዋለሁ። እስከዛሬም ስሙ ከብዶት አለመውደቁ ምን ያህል ይሉኝታ ቢስ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ሌላው ፌደራል ፖሊስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ እዝ ስር ሊሆን ነው። (ወይ ጠቅላይ ሚኒስትር… !) እርሳቸውም አንድ ቀን ይሄ ስም ከብዷቸው ክልትው እንዳይሉ ስጋት አለኝ… የሆነው ሆኖ ፌደራል ፖሊስ ድሮ በማን ስር ነበር… ብላችሁ የሪፖርተርን ዜና አንድ አረፍተ ነገር ስታነቡ ‘…ቀድሞ በፌደራል እና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር ስር የነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን…’ ይላችኋል። አርብቶ አደር ነው አባሮ አደር… ?እስቲ አሁን ፌደራል ፖሊስ እና አርብቶ አደርን ባንድ ላይ ተጠርንፈው ያስተዳድራቸው የነበረው ሰውዬ…. ምን አይነት ሙያ ነበረው ማለት ነው… የግብርና ባለሙያ ነበር ወይስ የወንጀል መከላከል ባለሞያ? አሃ ለካስ ዋናው የኢህአዴግን ፖሊሲ ማስፈጸሙ ላይ ነው እንጂ አማርኛ መምህርን ፊዚክስ እንዲያስተምር መመደብ ይቻላል… (በሳቅ መሞት አለ ደርቤ!)

በጥቅሉ ግን ፍትህ ሚኒስቴር ፈርሶ ድጋሚ ተቦክቶ ቢሰራ፤ ወይም ለሌላ ባለስልጣን ስራው ቢሰጥ እንዲሁ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢመሩት ወይም ፕሪዘዳንቱ ይምሩት ቢባል፤ አጠቃላይ ኢህአዴግ ፈርሳ ካልተሰራች በቀር ሰውም አትሆንም ለሰውም አትሆንም! (ፈርሳ ትሰራ የሚለውንም እኔ ቡቡ ስለሆንኩ ነው እንጂ እንደነገሯማ ፈርሷ የሰው ልጆች የማይደርሱበት ቦታ መጣል ነው ያለባት….) የምር አማረሩን እኮ!!! እስቲ ማን ቀራቸው ሁሉንም መደዳውን አስለቀሱን እኮ!!! ይዘገያል እንጂሁሌ እንዳስለቀሱ መኖር የሚሳካለት አስለቃሽ ጭስ ብቻ ነው!