በሃገራችን ለተከሰቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግሮች የኢሕኣዴግ የፖሊሲ ክምር በፍጹም መፍትሄ አይሆንም:: ‪


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በሃገራችን ለተከሰቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግሮች የኢሕኣዴግ የፖሊሲ ክምር በፍጹም መፍትሄ አይሆንም:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Ethiopiaprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Change‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሃላፊነት የጎደለው የወያኔ አገዛዝ ወንጀል ብንናገረው ብንናገረው ተዘርዝሮ አያልቅም::እየሰራን ነው እያለማን ነው በሚል የልማታዊ ዲሞክራሲ ሽፋን ላለፉት 25 አመታት ከፍተኛ መንግስታዊ ሽብር በሕዝብ ላይ ተፈጽሟል::ስልጣኑን በሞኖፖል የተቆጣጠረው ገዢው ፓርቲ እጅግ ለቁጥር የሚታክቱ አዋጆችን ደንቦችን እና ፖሊሲዎችን አውጥቶ እየተንቀሳቀስኩ ነው ቢልም ውጤታቸው ግን ከቀን ወደ ቀን የፖለቲካ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ቀውሶችን ከማስፋፋት ውጪ አንድም ለሕዝብ የፈየደው ያተረፈው ነገር የለም:: እንደጀመርን እንጨርሰዋለን የሚለው ልማት አዘል መፈክር ሕዝብን ከጥይት ከመጨረስ ዘሎ አያውቅም:: በሃገራችን ለተከሰቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግሮች የኢሕኣዴግ ፖሊሲ በፍጹም መፍትሄ አይሆንም::

Minilik Salsawi's photo.

ሕዝቡ ስር ነቀል ለውጥ እንደሚፈልግ ከ1997 ምርጫ ጀምሮ በተግባር በማሳየት ዛሬ ላይ ደርሷል:: የኢሕኣዴግ መልስ ግን ልክ እንደ ቅኝ ገዢ ለሕዝብ የጥይት እና የሽብር መልስ ብቻ በመስጠት ስልጣን የበቀለኞች መፈንጫ እንድንሆን አድርጓል::እንደ መንግስት ፖሊሲዎች ከመቀየር ሕዝብን ያሳተፈ ስርኣት ከመዘርጋት ይልቅ ዐዋጆች ሕዝብን መጨቆኛ ፖሊሲዎች ሕዝብን ማደኸያ መሳሪያ በማድረግ መፍትሄ አልባ አስተዳደሮችን ገንብቷል::ይህ ደግሞ በኢሓዴግ ፖሊሲዎች ሃገራችን ምን ያህል እንደተጎዳች ቁልጭ አድርጎ ስለሚያሳይ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግሮች በሕዝቡ ላይ እየፈነጩ ይገኛሉ::

በሃገሪቱ የገባው ረሃብ አገዛዙ ለዜጎች የሚሰጠው አትኩሮት አናሳነት ለተፈጥሮ አደጋ የአስቸኳይ ጊዜ ደራሽ ቡድን አለመኖሩ የባለስልጣናትን አምባገነናዊ ገበና ለመሸፈን የመልካም ገጽታ ግንባታ በሚል ሰበብ ዜጎችን በተለይ ሕጻናትን በረሃብ በመፍጀት ብቁ ዜጎች እንዳይፈጠሩ ድብቅ እኩይ አጀንዳ የመራመዱ ተግባር የወለደው የአገዛዙ ፖሊሲ ስለሆነ አገዛዙ ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ ካልቻለ ሃገራችን ለገባችበት ችግር መፍትሄ ሊገኝ እንደማይችል መገንዘብ ያስፈልጋል::

በኦሮሚያ በአማራ በትግራይ በጋምቤላ እና በደቡብ የተነሱት የሕዝብ ንቅናቄዎች የአገዛዙ የጎሳ ፖለቲካ ፖሊሲ የአገዛዙ በዘረፋ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ውጤቶች ናቸው::ሕዝቦች በአገራቸው ተዘዋውረው እንዳይሰሩ ጠፍንጎ በመያዝ ስራ አጥነትን እና ማህበራዊ ቀውስ እንዲፈጠሩ ያደረጉት አገዛዙ በድርቅና የሚከተላቸው ስኬት አልባ ፖሊሲዎች ናቸው::ካለሕግ እና ካለደንብ ባሻቸው መስመር ሃገሪቱን የሚያሽከረክሩ ባለስልጣናት የፈተሩት ነገር ቢኖር የፖለቲካ ጡጫ ሕዝብ ላይ ማሳረፍ እና የኢኮኖሚ ድህነትን ነው::ምንሊክ ሳልሳዊ ገዢው ፓርቲ በተጭበረበረ ፖለቲካ የገነባው የኢኮኖሚ ፖሊሲ አገሪቱን ለውጪ እዳ እና ለእርዳታ ለማኝነት ሲዳርግ ላለፉት 25 አመታት በየ አምስት አመቱ የተፈራረቁት የትራንስፎርሜሽን እና እድገት ፖሊሲዎች ሃሰተኛ ባለስልጣናትን እና የቁጥር ቁልልን ከመውለድ ውጪ በሃገሪቱ ብልጽግናን እና እድገትን አላመጡም:: የፖሊሲዎች በየጊዜው መውጣት ዜጎችን ለግድያ ለእስር ቤት እና ለስደት ከመዳረግ ውጪ አንዳችም አርኪ ተግባር አልታየበትም::

አዲሲቱን ኢትዮጵያ ለመገንባት ሁሉም ዜጎች የሚሳተፉበት ሕዝባዊ መንግስት ማቋቋም ግዴታ ነው::በኋላ ቀር የታሪክ እድፍ የሌላውን ስም እያጠፉ የራስን መልካም ገጽታ መገንባት የማይቻልበት በፕሮፓጋንዳ ቁልል ሕዝብን ማታለል የማይቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱን ሕዝቡ ራሱ በተግባር የመሰከረበት ተቃውሞ ያሰማበት ጊዜ ላይ ስለተደረሰ ስልጣንን ለሕዝብ ማስረከብ እንጂ የሚራመደው የአገዛዙ ፖሊሲ ለሕዝብ ሽብር ስለሆነ ሊሰረዝ ይገባዋል::በሃገራችን ለተከሰቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግሮች የኢሕኣዴግ ፖሊሲ በፍጹም መፍትሄ አይሆንም::መፍትሄው ስልጣን መልቀቅ እና በሰለጠነ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ የሕዝብን የበላይነት ማረጋገጥ ብቻ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬