ዶክተር መረራ ጉዲና ከሃገር እንዳይወጡ ተከለከሉ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ዶክተር መረራ ጉዲና ከሃገር እንዳይወጡ ተከለከሉ::
የወያኔ አገዛዝ ትላንትና ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ አሜሪካ ለመብረር በዝግጅት ላይ የነበሩትን የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲናን ከሃገር እንዳይወጡ ማገዱን የድርጅቱ የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል::
አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ “ቪዥን ኢትዮጵያ” (ራዕይ ኢትዮጵያ) በተሰኘ ተቋም ጋባዥነት በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሊጓዙ እንደነበር የጠቆሙት ዶ/ር መረራ፤ ሻንጣቸው ተፈትሾ ከተጫነ በኋላ “ፓስፖርቱ ላይ ያለውን ቁጥር የኛ ሲስተም ማንበብ አልቻለም” ተብለው ከቦሌ አየር መንገድ እንዲመለሱ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ “ፓስፖርቱን ኬሚካል ወይም ሽቶ አሊያም ዘይት ነክቶት ይሆናል” ብለውኛል ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ከአየር መንገዱ ከተመለሱ በኋላም ለኢምግሬሽን አቤቱታ ማቅረባቸውንና እስከ ትናንት ረፋድ ድረስ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ፓስፖርቱ የ3 ዓመታት የአገልግሎት ጊዜ እንዳለው የገለፁት ዶ/ር መረራ፤ ወደ ውጭ ሀገር መመላለስ ከጀመሩ ከ30 ዓመት በላይ እንደሆናቸውና ይህ አይነቱ ሁኔታ ሲገጥማቸው የመጀመሪያው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች” በሚል ርዕስ ለአንባቢያን ያቀረቡት መፅሃፍ፤ ሁለተኛ ህትመት መውጣቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሕወሓት አገዛዝ የሕዝብ ድጋፍ ያላቸውን የፖለቲካ መሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ በቁም እስር ላይ በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥበብ ክፍተኛ እንግልት እየፈጠረ ሲሆን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ላይ እንዲሁ ሕገወጥ መንግስታዊ ወንጀል ተፈጽሟል::#MinilikSalsawi