በአዲስ አበባና በዙሪያዋ መሬቶችን በእጅ አዙር ለመግዛት ሕወሓት ደላሎችን ሊያሰማራ ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአዲስ አበባና በዙሪያዋ መሬቶችን በእጅ አዙር ለመግዛት ሕወሓት ደላሎችን ሊያሰማራ ነው::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎AddisAbabaMasterplan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሕወሓት ስልጣኑን እና ጠበንጃን መከታ በማድረግ ከአዲስ አበባ እና ከተለያዩ አከባቢዎች ገበሬዎችን በማፈናቀል እጅግ በርካታ ዜጎችን ለችግር የዳረገ ሲሁን ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ዙሪያ በግብርና የሚተዳደሩ ነባር ነዋሪዎችን በሕግ እና ደንብ ሽፋን ማስተር ፕላን በማውጣት ለማፈናቀል ሲዘምት በደረሰበት ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ማስተር ፕላኑን እስከመሰረዝ ደርሷል::ሆኖም በእጅ አዙር ገበሬውን በተለያዩ ጥቅሞች በማታለል ደላሎችን አሰማርቶ ከውጪ አገር ባስመጣቸው የሕወሓት አባላት ስም መሬቶችን በመግዛት ለሪል ስቴት ሊያውላቸው መሆኑ ከነደፈው እቅድ ተገኝቷል::

Minilik Salsawi's photo.

ሕወሓት በአዲስ አበባ በተለይ በኦሮሚያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ የበላይነቱን ይዞ ሕዝብን እየገዛ እና እያስደነገጠ ለመኖር እየገደለ እና እያሰረ ስልጣኑን ለማስረዘም ከሚፈነቅላቸው ድንጋዮች አንዱ የትግራይ ተወላጅ የሆኑአ በውጪ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን እያሰባሰበ በማምጣት አስፈላጊውን የመንግስት ገንዘብ ፈሰስ በማድረግ በኢንቨስትመት ስም ከፍተኛ የሆነ የመሬት ቅርሚያ አድርጎ የመሃል አገር ለዋሪ ሕዝብን ገፍቶ በማውጣት የከተማ ታሪኮችን በማጥፋት የራሱን ልእለ ሃያል የኢኮኖሚ የበላይነት የመገንባት እቅዱን ውስጥ ውስጡን እየገፋበት ይገኛል::ሲሉ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ሰብስቦ ያመጣቸውን ካድሬዎቹን ነባር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመኖሪያ ቤት እጦት እየተቸገሩ ለካድሬዎቹ ግን በነፍስ ወከፍ ለአንድ ግለሰብ 3 እና 4 ኮንዶምኒየም ቤቶቹን በማደል ሕዝብ በችግር ተቆራምዶ በገዛ አገሩ ላይ ባይተዋር እንዲሆን አድርጎታል::

ለሕወሓት ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በሚገኙ አከባቢዎች የገበሬውን መሬት በአፈ ጮማ ደላሎች አስማምቶ ለመግዛት የእጅ አዙር እንቅስቃሴ የጀመረው ሕወሓት ደላሎቹ ገበሬዎቹን በተመለከተ አስፈላጊ ጥናት እንዲያደርጉ እና መረጃ እንዲሰበስቡ ለማድረግ ወደ ስራ የገባ ሲሆን አዘናግቶ ከሚያጠቃው ሕወሓት መሰሪነቱን የማያውቁ ምስኪን ግበሬዎች እንዳይታለሉ ሲሉ ለምኒሊክ ሳልሳዊ መረጃውን የላኩ ምንጮች ተናግረዋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬