በትግራይ መዲና መቐለ የባለ ባጃጆች ኣድማ ቀጥለዋል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በትግራይ መዲና መቐለ የባለ ባጃጆች ኣድማ ቀጥለዋል:: #Mekelle
ትናንት ዕሮብ መጋቢት14 /08 ዓ/ም በትግራይ መዲና መቐለ የባለ ባጃጆች ኣድማ ተመትቶ ውለዋል።
መንግስት ኣድማው በሃይል ለማንበርከክ ያለ ታፔላና ያለ ስምሪት ቦታ ለመስራት የሞከሩ ባለ ባጃጆች በክልሉ ልዩ ሃይል፣ የፖሊስ ና ትራፊክ ፖሊስ እያስገደደ ታርጋ ለመፍታት ሲሞክር “ኣናስፈታም” ያሉት በርካታ ወጣቶችና የባለ ባጃጅ ማህበራት ተወካዮች ናቸው ያሏቸው ከ30 በላይ ወጣቶች ኣስረዋል።
ለምሳሌ እኔ ታስሬበት ወይም ታግቼበት የነበረው የሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣብያ ሶስት ባለ ባጃጅ ወጣቶች እዛ እያለን ኣውቀናል። በነገራችን ላይ ትናንት ከ5:30 እስከ 10:30 እኔ ዓምዶም ገብረስላሴና የዓረና ፅሕፈት ቤት ሃላፊ ዘነበሲሳይ ታስረን ነበረ።
የእስር ተግባሩ በየ ክፍለ ከተማው ቀጥሎ መዋሉን ለማወቅ ችለናል።
የባጃጅ ሹፌሮች ኣድማ ዋነኛ ምክንያቶች
ሀ) የመንግስት ታፔላ ኣናደርግም ማድረግ ካለብንም በራሳችን ማህበሮች ቁጥጥር የሚደረግብን ብቻ መሆን ኣለበት።
ለ) በኣዲሱ የመንግስት ስምሪት ኣንሰራም በቆየው ስምሪት ነን የምንቀበለው የሚል ነው።
ኣድማው ለመጋቢት15 /08 ዓ/ም ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ኣስተዳደሩ በመጋቢት13 /08 የማህበራቱ ተወካይ ኣመራሮች በኣስቸኳይ እንዲሰበሰቡ ካደረጉ በኋላ ፦ ” የታፔላና የስምሪት ስራ እንድትጀምሩ ለ መጋቢት15 ኣስበን ነበር። ኣብዛኛው ባለባጃጅ እንዲቀበለው ለማስረዳት ግዜ እንድታገኙ ብለን ሁለት ቀን ጨምረን ለመጋቢት 16 እንዲዘገይ ኣድርገናል። እያንዳንዱ ማህበር ኣባላቱ እንዲያሳም።” ብለው በዛቻ መልክ ትእዛዝ ኣወረዱይላሉ።
ይሄ ቀጭን ትእዛዝ ተጭኖባቸው የወጡት የማህበራቱ ኣመራሮች ጥዋት መጋቢት 14 ሰብስበው የመንግስት ቀጭን ትእዛዝ ነገሯቸው።
ኣድማው መመርያው በሚታወጅበት መጋቢት 15 እንዲያካሂዱ ኣቅደው የነበሩ ቢሆኑም ይሄ ሲሰሙ ኣስቀድመው መተውታል።
“ታፔላ ኣናደርግም ካደረግንም መንግስት የሚቆጣጠረው ሳይሆን ማህበራቱ የሚቆጣጠሩትና የህዝብ መጨናነቅ ባለባቸው ኣከባቢዎች እየለየ ኣስገድዶ ሊያሰማራን ይችላል።”
መርያው የትራንስፓርት ህግ “ከ6 ሰው በታች የሚጭን ማንኛውም ተሽከርካሪ ታፔላ ኣይበጅለትም” ከሚለው ህግ የሚጣረስ ተቀባይነት የሌለው መመርያ ነው።” እያሉ ይሞግታሉ።
ኣድማ መቺዎቹ “የመቐለ ከተማ ከንቲባ ኣቶ ዳንኤል ኣሰፋ( የብሄራዊ ፀጥታና ደህነነት ሃላፊ የጌታቸው ኣሰፋ ታናሽ ወንድም) ከወር በፊት ሰብስቦን ነበር።
መመርያው በተመለከተ ተወያይተን ችግራችን በሚገባ ኣስረድተነዋል።
እሱም በወቅቱ 4 ኣስታራቂ ያለው ሃሳብ ኣካፍሎ በቀጣይ ውይይታችን የተሻለ ኣማራጭ ይዞ እንደሚመለስ ነግሮን ተለያየን።
፩) መስመር ብቻ ኣንሰራም ኣትበሉ
፪) ኮንትራት ብቻ ነው የምንሰራው ኣትበሉ
፫) ኮንትራት በፈረቃ መስራት ኣለባቹ
፬) ታፔላ የማህበራቹም ቢሆን እንድታደርጉ ተነጋግረን የተሻለ መፍትሄ እናመጣለን ብሎ ሸምግሎን ከሄደ በኋላ በኣሳሪው መመርያ ልዩ ሃይልና ፖሊስ ታጅቦ መጥቷል” ይላሉ።
ባለ ባጃጆቹ ከሁሉም በላይ ማህበራቸው ከመንግስት ንክኪ ነፃ እንዲሆንላቸውና ህዝቡና ራሳቸው በኣግባቡ ማገልገል ይፈልጋሉ ።
ኣድማ መቺዎቹ ኣዲሱ መመርያ ተቀብለው ከሰሩ ችግሩ ምንድነው?
“ሀ) ገቢያችን ይቀንሳል ፦ ከ2500 በላይ ባለ ባጃጆች ገቢ ይቀንሳል፣ ቤተሰብ ይበተናል።
ለ) ከማንኛውም እንቅስቃሴ ( በምሳሰዓት፣ ሓዘን፣ ሰርግ፣ ለቤንዚን ለመግዛት፣ ጋራዥ ለማስፈተሽ ወዘተ በነፃነት እንዳንሳተፍ እስረኞች ያደርገናል።
ሐ) ባለ ባጃጅ በመስመር ብቻ የሚሰራ ከሆነ ለቤንዚን ኪሳራ ተዳርጎ ከስሮ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
መ) በ20 ለ 80 የሚባል የብድር ኣግባብ ከመንግስት ተበድረን የምንሰራ ወጣቶች ከስረን እዳ እናተርፋለን።
ሰ) በእዳ ከውድድር ውጭ ከሆንን ወደ ወንጀልና ኣልባሌ ቦታ እንድንገባ እንገደዳለን። ግማሹም እንደ ወንድሞቹ እግሩ ወደ ስደት ያመራሉ፤ ይታረዳል፣ በበረሃ ይሞታል፣ በባህር የኣሳ እራት ይሆናል ስለዚ ይሄ ኣሰቃቂ ድርጊት እንዲደርስብን ኣንፈልግም፣ ኣገራችን ሰርተን መኖር ነው የምንፈልገው።” ይላሉ።
መንግስት ከዚህ መምርያው ምን ጥቅም ይገኛል ብሎ ያስባል?
መንግስት የመመርያው ሁለት ጠቃሚ ያላቸው ነጥቦች ይናገራል
1) በደፈናው ባጃጆች ስርዓት እንዲይዙ ያደርጋል ይላሉ። ያፈረስነው ስርኣት የት ኣለ ሲባል ዝርፍያ( ሃንግ) ኣለ ይሉናል” ይላሉ።
ዝርፍያ በባጃጅ የሚደረገው ነው የሚበዛው በየሰፈሩ፣ በየ ድልድዩ፣ በየ ጨለማው የሚደረገው ነው?
ይሄ ወጣት ከስራ ውጭ ስታደርጉ ዝፍያ ይቀንሳል ብላቹ ነው የምታስቡት? ብለን ስንጠይቃቸው መልስ የላቸውም።
ማምለጫ መንገዳቸው “ለቁጥጥር እንዲመቸን” የሚለው ጥቅሉል ሃሳብ ያቀርባሉ።
እኛ የተረዳነው መንግስ ወጣቱ በኣገሩ ስርቶ መኖር ኣይፈልግም፣ ኣቅም ያለውና በገቢ ራሱ የቻለ ወጣት በከተማው ማየት ኣይፈልግም፣ ራሳችንም ማሕበራችንም በቁጥጥር ስር ሊያውለን ይፈልጋል።
በጣም የሚያሳዝነው ድርጊት ደግሞ በኤፍ ኤሞ FM ራድዮዎቻቸው ስማችን በማጥፋት ከህዝቡ ሊያጣሉን እየሞከሩ ነው። ኤፍ ኤሞች የኛ ጉዳይ ከኛ ማግኘት ነበረባቸው።
እኛ ከ2500 በላይ ወጣት ሹፌሮች እና ኣከራዮች ኣለን። እኛ የምንመራቸው ቤተሰቦች ኣሉ፣ እኛ የምናገለግለው ህዝብ ኣለ ስለዚ ቢያውቁት ህዝብ ማለት እኛ ነበርን። ይላሉ።
በኣሁኑ ሰዓት ከ30 በላይ ባለ ባጃጆች በየ ክፍለ ከተማው ታስረዋል፣ ሁላችንም ሊያስሩን ይችላሉ ይሄ መመርያ ትተነዋል ብለው እስኪ ገልፁ ኣድማው ይቀጥላል።
ተስፋ ቆርጠን ካገራችን የምንሰደድ ከመሰላቸው ደግሞ ተሳስተዋል እኛ ካገራችን ንቅንቅ ኣንልም ታግለን መብታችን እናስከብራለን እንጂ…!” ሲሉ ገልፀውልኛል።
ኣብዛኛው ባለ ባጃጆች ዲግሪ ያላቸውና የተማሩ ወጣቶች ናቸው።
የሁሉም ወጣቶች ኣቋም መንግስት መመርያ ሰርዣለው ካላለ ኣድማው ይቀጥላል። ይሄ መረጃ ያካፈሉኝ ከእስር ቤት ከተለቀቅኩ ያገኙኝ ባለ ባጃጅ ወጣቶች ናቸው ናቸው።
የእስራችን ምክንያትም ከባለ ባጃጆቹ ላለማገናኘት እቅድ ነው።
* መንግስት የባጃጅ ኣስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ( የሚሰሩበት ሰዓት ለመገደብ) ለማወጅ እቅድ እንዳለውም መረጃው እንደደረሳቸው ይገልፃሉ።
#BAJAJ_Protest_Mekelle_Tigray_Ethiopia
* ትግራይ ኢህኣዴግ የሚፈለፍላቸው ኣፋኝ መመርያዎች መመኮርያ ኣይጥ ኣትሆንም…!
ነፃነታችን በእጃችን ነው
it is so.