የወያኔ‬ መሪዎች ጦራቸውን ወደ ኮንሶ በመላክ ከተማዋን በወታደራዊ ቁጥጥር ስር አድርገዋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News
መጋቢት 13 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (March 23, 2016 NEWS)
‪#‎የዳንሻ‬ ከተማ በትግራይ ሚሺያዎችና በወያኔ ጦር ስትወረር ሕዝቡም የመኪና መንግደኦችን በመዝጋት ወደ ጎንደርና ሁመራ የሚወስዱ መንገዶችን የዘጋ ሲሆን የታስሩት የሕዝብ ወኪሎች እንዲፈቱ በመጠየቅ የዳንሻን ፖሊስ ጣቢያ መክበቡ ታውቋል።
‪#‎የወያኔ‬ መሪዎች ነፍሰ ገዳይ የሆነውንና አግአዚ የተባለውን ጦራቸውን ወደ ኮንሶ በመላክ ከተማዋን በወታደራዊ ቁጥጥር ስር አድርገዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ሕዝቡ የሚፈልገው ለጥያቄው ሰላማዊ ምላሽ እንጅ እስር፤ የወታደር ጋጋታ እና የነፍስ ገዳይ ጦር ክምትት እንዳልሆነ በመግለጽ የወያኔ አፋኝና በጨመረ ቁጥር የሕዝብም የመታገል ቁርጠኛነት ይጨምራል በማለት ይናገራሉ።
‪#‎ለዓመታት‬ ምንም ዓይነት ጥገናና ዕድሳት ያልተደረገለት ሲገነባ አርባ አምስት ሚሊዮን ሜትር ኪዮቢክ ውሃ እንዲይዝ ተድርጎ የተሰራው የለገዳዲ ግድብ ዛሬ ላይ አንድ ሚትር ወይንም 62 ሺ ሜትር ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መቀነሱ ታውቋል። የወያኔ ባለሥልጣናት ውሃ በፈረቃ ይሆናል ማለታቸው ወትሮም በፈረቃ የነበረው ውሃ ጭራሽኑ ይጠፋል ማለታቸው ካልሆነ በስተቀር ውሃ በፈረቃ ሌትና ቀን ሳይጠበቅ የመጣበት ጊዜ ተረስቷል የሚሉ ነዋሪዎች ብዙ ናቸው።
‪#‎ወያኔ‬ የአዲስ አበባ አጎራባች ከተሞችን ወደ አዲስ አበባ በማስተር ፕላን ለመጠቅለል የወጣውን ዕቅድ በመቃወም ለሞቱ ለተንገላቱ ለታሰሩና ለተደበዱ ሰዎች የሰብዓዊ መብታቸው መደፈሩን ለማጣራት አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር የተባለው ካድሬ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪና መርማሪ ብሎታል። አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር በወያኔ የምርጫ ቦር ውስጥ ለሰራው ተንኮልና ደባ ወያኔ በኮሚሽነርንት ማዕረግ የሰብአሰኢ መብት ጥሰትን ትመላች ማድረጉ ይታወቃል።
‪#‎ሰሞኑን‬ ለትግራይ ክፍለ ሀገር ለመስኖ ስራ በማለት የውሃና የኃይል ሚኒስትር የሰጠው 30 ሚሊዮን ብር መዘሩፉ ታውቋል። ገንዘቡ የትግራይ ክፍለ ሀገር የውሃና የግድብ ቢሮ ኃላፊ ጌታቸው የተባለው የትግራዩ ገዥ የፀጋዬ በርሄ የእህት ልጁ እንዳስረቀው ታውቋል።
‪#‎በቤልጅየም‬ ዋና ከተማ በብራስልስ በአውሮፕላን ማረፊያና በባቡር ጣቢያ የፈነዱት ቦምቦች ጉዳት አደረሱ
‪#‎የናይጄሪያ‬ የነዳጅ አምራች ኩባንያ 25 ቢሊዮን ዶላር ለመንግስት ማስገባት የነበረበትን ገንዘብ አለማስገባቱ ተጋለጠ
‪#‎በአልጀሪያና‬ በማሊ የታጠቁ አጥቂዎች በጸጥታ ኃይሎች ተገደሉ
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to /read/listen detail news click below)
To Read: http://www.finote.org/news.html
To Listen PART 1: http://finote.org/March22EVE_Hr1.mp3
To Listen PART 2: http://finote.org/March22EVE_Hr2.mp3