የትግራይ ኣስተዳደር በ30 ሚልዮን ብር የሙስና ክስ ሊቀረበበት ነው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የትግራይ ኣስተዳደር በ30 ሚልዮን ብር የሙስና ክስ ሊቀረበበት ነው።
።።።።።።።
የውሃና ኢነርጂ ምኒስቴር ለትግራይ ክልል መስተዳድር የ30 ሚልዮን ብር ሙስና ክስ ሊያቀርብበት ዝግጅቱ ማጠናቀቁ ታውቋል።
የ30 ሚልዮን ብር ክሱ በራያ ለመስኖ ስራ እንዲውል ተብሎ በፌደራል የውሃና ኢነርጂ ምኒስቴር በጀት ተይዞ የነበረ ሲሆን ምንም ሳይሰራበት የተዘረፈ ብር ነው።

ምኒስቴሩ በጀቱ የውሃ ጉድጓድ ተቆፍረው ገበሬዎች ለተለያየ የመስኖ ስራዎች የሚያገለገሉባቸው ፕላስቲክ ቱቦላሪዎች ከውጭ እንዲገዛ የታቀደ ሲሆን በወቅቱ የትግራይ ክልል የውሃና መኣድን ቢሮ ሃላፊ የነበረው ኣቶ ጌታቸው የተባለ የኣቶ ፀጋይ በርሀ የእህታቸው ልጅ ጥራት የጎደለው እቃ ካስገባና ከጥቅም ውጭ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ ብሩ ይዞ ጃፓን ኣገር መግባቱ የሚታወቅ ነው።
ብሩ በመዘረፉ ምክንያት የመስኖ ስራው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ የሆነ ሲሆን ብሩ ዘርፎ ጃፓን የገባው የኣቶ ፀጋይ በርሀ የእህት ልጅ የሆነው ኣቶ ጌታቸው በቁጥጥር ስር ለማስገባትም ምንም ዓይነት ሙከራ ኣልተደረገም።
ምኒስቴሩ ኣሁን በትግራይ ክልል መስተዳድር እየመሰረተው ያለው ክስ 30 ሚልዮን ብሩ ሙስና ዙርያ የወቅቱ የትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪዎች እጅ ኣላቸው የሚል ነው።
የትግራይ ክልል በፌደራልና በክልል መንግስት የሚበጀት በሚልዮን የሚገመት ብር በሃላፊዎች እየተዘረፉ ፕሮጀክቶች ተጀምረው ሳይጠናቀቁ በቁም የሚቀሩባት ክልል ናት።
በኣሁኑ ወቅት ህወሓትና ሙስና፣ ሙስናና ህወሓት ተነጣጥለው የማይታዩ የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገፆች መሆናቸው ተረጋግጠዋል።