እውን ኢህአዴግ ከግንባርነት ወደ ውህድ ፓርቲነት ይሸጋገራል?


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


እውን ኢህአዴግ ከግንባርነት ወደ ውህድ ፓርቲነት ይሸጋገራል? Tadesse Biru Kersmo

ስለዚህ ጉዳይ መወራት ከጀመረ ዓመታት ቢቆጠሩም እንደኔ ግምት ተግባራዊ የሚሆን አይመሰለኝም፤ በድፍረት ካደረጉት ደግሞ የሥርዓቱን ውድቀት ያፋጥናል። ለዚህ ምክንያቶቼ ሦስት ናቸው።

1) የህውሓትን ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ሥራ አስፈፃሚ እንዳለ የውህዱ ፓርቲ ማዕከላዊና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ካልሆነ አሁን ያለውን የህውሓት የበላይንትን ማሰጠበቅ ይቸግራለ። ተዋሀድን እያሉ የህውሓትን ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ሥራ አስፈፃሚ እንዳለ የውህዱ ፓርቲ ማዕከላዊና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማድርግ ደግሞ የሚቻል አይመሰለኝም። ኢህአዴግ በህወሓት የሚመራ መንጋ እንጂ ውህድ ፓርቲ ሆኖ መቆም የሚችል አይደለም።

2) ኢህአዴግ ራሱ ያረቀቀውን “ህገመንግሥት” ተብሎ የሚጠራውን ሰነድ መምሰል አለበት። በህገመንግሥቱ ኢትዮጵያ በዘር የተደራጁ ስብሰቦች ድምር ነች — ኢህአዴግም እንደዚያው። ኢህአዴግን ወደ ውህድ ፓርቲ ቀየሩት ማለት ህገመንግሥቱን ችግር እንዳለበት አመኑ ማለት ነው። ይህን ለማደረግ ድፍረት ያላቸው ሰዎች ኢህአዴግ ውስጥ አሉ ብዬ አላምንም። ለታይታ ብቻ ካደረጉት አሁን ካለው የባሰ ሽባ ድርጅት ይመሠርታሉ፤ በዚህም ፍፃሜያቸውን ያቀርባሉ።

3) ውህዱን ፓርቲ አገራዊ መሪ ያስፈልገዋል። አስካሁን ኢህአዴግ ክልላዊ እንጂ አገራዊ መሪ ማውጣት አልቻለም። የክልል መሪዎች የፌደራል ስልጣን ሲይዙ በኮታ ስሜት ነው እንጂ ወጥ በሆነ መንገድ አይደለም። ኢህአዴግ ውስጥ የአገራዊ መሪ እጦት ድሮም የነበረ ችግር ቢሆንም ከመለስ ህለፈት በኋላ ተባብሷል። ድሮ የለቀቁት የህወሓት ሰዎችን (እነ ስየ አብረሀን) ለመመለስ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ያለው ይህንን ቀዳዳ ሊሸፍኑ ይችላሉ ብለው ስለሚያሰቡ ይመስለኛል። ግን አነሱንም ቢሆን የምናውቃቸው በክክልል ነፃ አውጭነት በመሆኑ ቀዳዳው መሸፈን የሚችሉ አይሆኑም።

ከላይ በዘረዘረኳቸው ሦስት ምክንያቶች ሳቢያ ኢህአድግን ውህድ ፓርቲ የሚያደረጉት አይመሰለኝም፤ በድፍረት ካደረጉት ግን በወንጭፍ የሚገነደስ ጎልያድን ይሰሩልናል።