ሰበር ዜና : በዳንሻ የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ ባዶ እጃቸውን ባሉ የወልቃይት አማሮች ላይ እየተኮሰ ይገኛል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሰበር ዜና : በዳንሻ የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ ባዶ እጃቸውን ባሉ የወልቃይት አማሮች ላይ እየተኮሰ ይገኛል::
በዳንሻና በሶሮቃ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ አለ፡፡ የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ ከሦስት ቀናት በፊት አቶ ሊለይ ብርሃነ የተባለን የወልቃት አማራ አፍኖ ወስዶ የት እንዳደረሰው ባለመታወቁ ምክንያት በሕዝቡ በተቀሰቀሰ ቁጣ በዚህ ሰዓት በአካባቢው ችግር እንደተፈጠረ በስልክ እየተነገረኝ ነው፡፡ሲል የቀለም ቀንድ ጋዜጣ አዘጋጅ ሙሉቀን ተስፋው ጽፏል::
ወዳጆች ሆይ የታጠቀ የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ ባዶ እጃቸውን ባሉ የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ላይ እየተኮሰ ከቦናል ብለውኛል፡፡ ይህ ችግር ከፍተኛ የሕዝብ እልቂት ከመድረሱ በፊት ለሚመለከታቸው አካላት እንዳደርስላቸው በተደጋጋሚ በስልክ አሁንም አሁንም እየተነገረኝ ነው፡፡ እኔ ለማንም ማድረስ አልችልም፡፡ አሁን ሌሊት ነው፡፡ ይህን መልእክት የምታነቡ ሁሉ በዜጎች ላይ አላስፈላጊ እልቂት እንዳይደርስ የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ እጠይቃለሁ፡፡ ሙሉቀን ተስፋው እንዳለው በስልክ ከሚነገረኝ አንጻር ከጠዋት አምስት ሰዓት ጀምሮ በፖሊስ ጣቢያ የተሰበሰቡ የወልቃይት አማሮች በፖሊስ ተከበው ችግር ውስጥ መሆናቸውን ነው፡፡ መልእክቱን በቀላሉ ባንመለከተው ደጋግሜ አሳስባለሁ፡፡ #MinilikSalsawi