ፍፁም ግራ የሚያጋባ የሀብት እድገት (ቴዎድሮስ ጌታሁን) – ከአስተማሪነት ወደ ቢሊየነርነት
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ፍፁም ግራ የሚያጋባ የሀብት እድገት
(ቴዎድሮስ ጌታሁን)
ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ሪፖርተር ጋዜጣ ያወጣውን አንድ ፅሁፍ አንብቤ እንደጨረስኩ ግራ ተጋባሁ፤ ፅሁፉን ሙሉ ለሙሉ አንብቤ ከጨረስኩ በኋላ ሦስት ሊሆን ይችላል ከሚል መደምደሚያ ሀሳብ ላይ ደረስኩ። አንድ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ሰው፣ የሴትየዋን ንግግር በደንብ አሳምሮ አልፃፈውም ሁለት ሴትዮዋ ያለፈችበትን የህይወት መንገድ በደንብ የማስረዳት ችሎታ የላትም ሦስት ከእያንዳንዱ ሀብት ጀርባ አንድ የተሰወረ ሚስጥር አለ የሚል መደምደሚያ ላይ ደረስኩ። ምን አልባት እናንተ ከዚህ ውጪ ከታዘባችሁ ፍርዱን ለናንተ ልተው በሚል ከቃለ መጠይቁ መሀል ቃል በቃል የወሰድኩትን ሀሳብ ላስነብባችሁ ወደድኩ
እንደ መግቢያ
የባለሃብቷ ሙሉ ስም ወ/ሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ
ስራ ነጋዴ፣ ባህርዳር ከተማ ጣና ዳር የሚገኘው ባለ አምስት ኮከብ “ግራንድ ሪዞርት ባለቤት” (በሀገሪቱ የመጀመሪያው ትልቅ ሆቴል እንደሆነ ይታወቅ)
ጠያቂ፦ አስተማሪ እንደነበሩ ሰምቼያለሁ?
ወ/ሮ ትልቅ ሰው ፦ አዎ ነበርኩኝ ከትምህርት በኋላ ለሰባት ዓመታት ከ 1983- 90 ድረስ የመንግስት ት/ቤት አስተማሪ ነበርኩ
ጠያቂ፦ ከ አስተማሪነት ወደ ንግዱ ዓለም እንዴት ሊገቡ ቻሉ?
ወ/ሮ ትልቅ ሰው፦ የ አስተማሪነት ህይወት በጣም ከባድ ነው የአካባቢዬ ልጆችና ጉዋደኞቼ ወደ ንግዱ ዓለም እንድገባ ሁልጊዜ ይገፋፉኝ ነበር መጀመሪያ ወደ ሰላሳ ሰባት ሺ ብር ገዳማ እቁብ ሰብስበው ሰጡኝ፤እሱን ከፈልኩ ቀጥሎ ሰባ ሺ ከዛም መቶ እና ሁለት መቶ ሺ ብር እያደረጉ ሰጡኝ፤ ያን ሰብስቤ ከቻይና ልብስ እያመጣሁ ለመነገድ ሄድኩኝ ቢሆንም ስራውን አልወደድኩትም ጠዋት ተነስተን ስንዞር ውለን ማታ ነው የምንገባው አንድ ቀን ቤጅንግ በረንዳ ላይ ተቀምጬ አለቀስኩ አምላኬ ሆይ የተረጋጋ ስራ ስጠኝ ብዬ ለመንኩት ከዛ አንድ መኖሪያ ቤት ገዛሁ እሱን ኮላተራል አድርጌ ባንክ ተበደርኩ፣ከዚያ ትራስንፖርት ቢዝነስ ውስጥ ጊቢ ሲሉኝ አውቶቢስ ገዛሁ ከዚያ ሦስት ሆኑ። ጠዋት ጋቢ ለብሼ አውቶቢስ ተራ እሄድ ነበር ከዚያ ወንድሞቼን አምጥቼ እነሱን ቲኬት ቆራጭ አደረኩ። ይህም ስራ በጣም አስቸጋሪ ነበር። ከዚያ እንደምንም ከሰራሁ በኋላ አንድ የጭነት መኪና ደገምኩ። ከቢዝነስ ሰዎች ጋር ተመካክሬ ቦቴ ይሻላል ሲሉኝ ሦስት ቦቴ ገዛሁ፣ ከዚያም ሦስት ቦቴዎች ጨመርኩ በሰፊው ወደ ትራንስፖርት ስራ ገባሁ። ስራውንም ወደድኩት በእርግጥ ስራው ፈታኝ ነው ሹፌሮች አደገኞች ናቸው እኔ አንድ ዘዴ ስዘይድ እነሱ ሌላ እየዘየዱ እንዲሁ ስንዋደቅ ለስራ ጎበዝ እንደሆንኩ የሚያውቅ አንድ ጓደኛዬ ቻይኖች የያዙት ስራ አለ አለኝ። ከዚህም ከዚያ ብዬ ከባንክ ተበድሬ አምስት ሚሊየን ቀብዱን ከፈልኩና አርባ ገልባጭ ገዛሁ በአንድ ጊዜ አርባዎቹም ገቡልኝ።ኮንስትራክሽን ጥሩ ሰራሁ እንደገና ሃያ የጭነት መኪና ገዛሁ፣ዶዘሮችም ገዛሁ በኋላ ቦቴ ስገዛ ተዛማጅ ስራ ማደያ መስራት አለብኝ ብዬ በደብረ ማርቆስ የማደያ ቦታ ሰጡኝ ከዚያ ይሄን በሀገሪቱ እጅግ ግዙፍ የሆነውን ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ገነባሁ።
——————-ተፈፀመ—————-
እንግዲህ በቀላሉ ከአስተማሪነት ወደ ቢሊየነርነት የተቀየረችበት የሀብቱ ሚስጥር ይኸው ነበር።