በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Harerge‬ ‪#‎EPRDF‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ግፍ በደል ጭቆና በገዛ መሬቱ ላይ ብዝበዛ ያንገፈገፈው የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞውን አቀጣጥሎ እንደቀጠለ መሆኑን ከኦሮሚያ ክልል የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::በትምህርት ቤቶች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በገበያ ስፍራዎች ሕዝቡ ድምጹን ማሰማቱን በመቀጠል ጭቆና በቃን ሞት ለጨቋኞች ማለቱን ቀጥሏል::ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ስም ዝርዝር ተያይዟል::

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በሚዳጋ ሎላ በዛሬው እለት ከአምስት ሰአት ጀምሮ ተቃውሞ ሲደረግ የዋለ ሲሆን ዛሬ ምንም እንኩዋን የገበያ ቀን ቢሆንም የመሸጥ እና የመግዛት ሂደቱ ተስተጋጉሎ ወሎዋል በዚህ ተቃውሞ የሕወሓት አገዛዝ በወሰደው እርምጃ በርካቶች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል አምስት ሰዎችን ታስረዋል:: የወያኔ አገዛዝ አንድ ከባድ የጦር ካሚዮን መኪና ሙሉ የአጋዚ ጦር ተቃዉሞውን ለመበተን በገበያው ስፍራ እንደራገፈ ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል

የታሰሩት አምስቱ ሰዎች ስም ዝርዝር :-
1/ Calaa Jiree
2/ Aarif Abduramaan
3/ Mahamadi A/Muummee
4/ Danbaloo Mahamad fi
5.Gammachuu Aammee

በሕወሓት አገዛዝ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የጭቆና እና ኢሰብዓዊ ድርጊት በመቃወም አሜሪካ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው ታስረው የነበሩ እና በአሁን ሰዓት ክስ ተመስርቶባቸው ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ስም ዝርዝር

1 ሶሬሳ ደሜ 4ኛ ዓመት ሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ
2 ቢሊሱማ ብርሃኑ 2ኛ ዓመት ኢኮኖሚክስ ተማሪ
3 ጉዲና ተስፋዬ 2ኛ ዓመት ማኔጅመንት ተማሪ
4 እሸቱ ደጀኔ 2ኛ ዓመት ኢኮኖሚክስ ተማሪ
5 ደበላ ፈይሳ 4ኛ ዓመት ኢንጅነሪንግ ተማሪ
6 ባቴ ለሚ 2ኛ ዓመት ማትስ ተማሪ
7 አለሙ ኦላኒ 2ኛ ዓመት ኢኮኖሚክስ ተማሪ
8 ገመቹ ከበደ 1ኛ ዓመት የኦሮምኛ ቋንቋ ተማሪ
9 አህመድ መሃመድ 5ኛ ዓመት ኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ
10 ሂንሳረሙ ቦጋለ 3ኛ ዓመት አካውንቲንግ ተማሪ
11 እጅጉ ቀበታ 2ኛ ዓመት ኢኮኖሚክስ ተማሪ
12 ሸለመ ገመቹ 2ኛ ዓመት ኢኮኖሚክስ ተማሪ
13 ገመቹ ሃይሉ
14 መርሻ ባይሳ 2ኛ ዓመት ኢኮኖሚክስ ተማሪ
15 ተስፋዬ ጌቱ 3ኛ ዓመት ማኔጅመንት ተማሪ
16 ተሬሳ አስናቀ 2ኛ ዓመት ኢኮኖሚክስ ተማሪ
17 ተስፋዬ መኮንን 2ኛ ዓመት ኢኮኖሚክስ ተማሪ
18 ዳንኤል አብዲሳ 2ኛ ዓመት ኬሚካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ
19 ጉታ ባይሳ 2ኛ ዓመት ኬሚካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ
20 ብርሃኑ በዳዳ 1ኛ ዓመት ፐብሊክ አድሚንስትሬሽን ተማሪ

Minilik Salsawi's photo.