ጉዳቸው አያልቅም! በአንድ ራስ ሁለት ምላስ – ራእይ አልባ ባለስልጣናት እና መንግስት አልባዋ ኢትዮጵያ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጉዳቸው አያልቅም! በአንድ ራስ ሁለት ምላስ – ራእይ አልባ ባለስልጣናት እና መንግስት አልባዋ ኢትዮጵያ
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎HMD‬ ‪#‎EPRDFHOAX‬ ‪#‎Ethiopiafamine‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

“አስረአንድ በመቶ አድገናል በምግብ እህል ራሳችን ችለናል::” አርከበ እቁባይ የጠሚው አማካሪ
“በድርቁ ለተጎዱ ዜጎች ተጨማሪ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይደረግለን::” ሃይለማርያም ደሳለኝ
“ለረሃቡ እርዳታ ለማግኘት እስረኞች መፍታትን እንደ መደራደሪያ አቅርቧል::” በአ.አ የአውሮፓ ዲፕሎማቶች
Minilik Salsawi – Ethiopian DJ በአንድ ወቅት በፊያሜታ ጋዜጣ ላይ ኢሕኣዴግ የሚባል ፓርቲ እና ባለስልጣኖቹ ራእይ አልባ እንደሆኑና ሃገሪቷን ወደ አዘቅት እየወረወሯት እንደሆነ በጻፍኩ ጊዜ አንድ ቱባ የተቃዋሚ አመራር የእድገት እቅዱ ረቂቅ እሕኣዴግ ጥሩ አድርጎ እንደከተበው በመግለጽ ሊከራከሩኝ ሞክረው ነበር::እስከዛሬ ግን የምናየው ነገር በእቅድ ከመያዝ እና በራእይ ከማለም ውጪ አንድም ጠብ ያለ ነገር አላየንም::አርከበ እቁባይ አስረአንድ በመቶ አድገናል በምግብ እህል ራሳችን ችለናል ባሉ ሳምንት ሳይሞላ ሃይለማርያም ደሳለኝ በድርቁ ለተጎዱ ዜጎች ተጨማሪ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንዲያደርጉ ለአለማቀፉ ማህበረሰብና ለለጋሽ ተቋማት ከትናንት በስቲያ ጥሪ ማቅረባቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል::

በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ማለት ይህ ነው::አርከበ ደረቱን ነፍቶ በብሎምበርግ ቃለመጠይቁ ላይ ምራባውያን እና ቻይና ባለፉት 10 አመታት ያላስመዘገቡትን እድገት እንዳስመዘገበ በምግብ እህል ራስን መቻል ደረጃን እንደታለፈ እና ትልቅ የኢኮኖሚ እድገት ስኬት እንደተመዘገበ የተፋው ዲስኩራዊ ምራቅ ሳይደርቅ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተቀብሎ አርከበ ውሸታም መሆኑን አጋልጧል:: ሃይለ ማርያም ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ፣ እስካሁን ከአለማቀፉ ማህበረሰብ የተደረገው እርዳታ በጣም አነስተኛ ከመሆኑም በላይ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው በአብዛኛው ዘግይቶ እንደሆነ ተናግሯል:: ዩኒሴፍን የመሳሰሉ አለማቀፍ ተቋማት በአፋጣኝ ተጨማሪ እርዳታ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል ሲል በሌሎች የአለማችን አካባቢዎች የተከሰቱት ቀውሶች እንዳሉ ሆነው አለማቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ችግር ችላ ማለት የለበትም ያለው ሃይለማርያም፣ አገሪቱ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 750 ሺህ ያህል የጎረቤት አገራት ስደተኞችን እንደማስጠለሏ፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ ተጨማሪ ድጋፍ ሊያደርግላት ይገባል ብለዋል – ለአሶሼትድ ፕሬስ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትና ለጋሾች ከ10 ሚሊዮን በላይ የአገሪቱ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋት ሲሆን ድርቁ ያስከተለውን ችግር ለመቋቋም ከ1.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ያስፈልጋል::

ችላ አትበሉን የምራባውያን ያለህ የሚለው የወያኔ አገዛዝ ለረሃቡ ድጋፍ የሚደረግ ከሆነ የተወሰኑ እስረኞችን ለመፍታት ከምጥራባውያን ጋር ለመደራደር መዘጋጀቱን የአውሮፓ ሕብረት ዲፕሎማቶች አከባቢ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ::በአዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶች እንደሚሉት የወያኔ አገዛዝ የሕዝቡት 24 በመቶ እስር ቤት እንዳሰረ በሃገር ውስጥ ከተሰበሰቡ መረጃዎች ዋቢ ሲያደርጉ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ይታያል የተባሉ ግን ሁለት በመቶ እንደማይሞሉ ተናግረዋል::በተለያዩ እንደ ጸረ ሽብር ባሉ አደገኛ ሕጎችን ዜጉቹን ያስራል ሲሉ የወያኔ አገዛዝን ዲፕሎማቶቹ ይነቅፉታል::በተላያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች ከፍተና የሆነ ሕዝብ ድርቅ እና ረሃቡን በመሸሽ እየሞተ እየተሰደደ እና እየተፈናቀለ ይገኛል::አገራችን እና ሕዝብናችን የወያኔ አገዛዝ በሚከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ሲሆኑ አገዛዙም አጣብቂኝ ውስጥ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.