የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ለጠ/ሚኒስቴር ለኃ/ማሪያም ደሳለኝ ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መፃፋቸውን ተዘገበ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Abdalla Abdalla's photo.

በመጋቢት ወር አጋማሽ ላይ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁት የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት በመግለፅ ለጠ/ሚኒስቴር ለኃ/ማሪያም ደሳለኝ ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መፃፋቸውን በዝ ፊድ ኒውስ የተሰኘ ጋዜጣ ዘገበ ።
የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲያደርግ የቆየው ጥረት ውጤት አለማምጣቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤውን እንደጻፉ በዝ ፊድ ኒውስ የተሰኘ ጋዜጣ በዘገባው አስፍሯል። የጠቅላ ሚኒስትሩ ዴቪድ ካሜሮን የኢትዮጵያ ጉብኝት የነበረው በቅርቡ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ከተለያየ አካላት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ ግፊት እንደያደርጉ የቀረበላቸውን ከ130ሺ በላይ ፊርማ ተከትሎ መሆኑም ተገልጿል።
የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ ቢቆይም የተፈለገው ውጤት ሊገኝ አለመቻሉን ሬፕሪቭ የተሰኘ የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በድረ-ገጹ ዘግቧል። የጥረቱን አለመሳካት ተከትሎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያላቸውን ስጋት በመግለጽ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማሪያም ደሳለን ሁለት ጊዜ ደብዳቤ መጻፋቸውን ጋዜጣው የሃገሪቱን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
የእንግሊዝ ጠ/ሚኒስቴር ዴቪድ ካሜሮን ለጠ/ ሚኒስቴር ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በፃፉት ደብዳቤ ሁለቱ ሃገራት ካላቸው የጠበቀ ግንኙነት አንፃር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ዙሪያ ሲደረገ የቆየው ውይይት ፍሬ አለማፍራቱ ቅሬታን እንደፈጠረባቸው በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።
የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ አካላት የቀረበባቸውን ግፊት ግምት ውስጥ በማስገባት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫናን እንዲያደርጉ በማሳሰብ ላይ መሆናቸውም ተዘግቧል። ሪፕሪቭ የተሰኘውን የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጨምሮ በርካታ አካላት ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የደህንነትና የጸጥታ ድጋፍ እንድትቋረጥ ሲያሳስቡ መቆየታቸውም የሚታወቅ ነው።

BBN