ሁልጊዜ ብሶት ማሰማት ደግሞ አድካሚ ነው።የለዉጥ፣ የመፍትሄ፣ የመልካም አማራጭ ፖለቲካ እንጂ የብሶት፣ የዘረኝነት ፖለቲካ አሰልቺ ሆኗል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Girma Kassa : በአገራችን ጉዳይ ትንሽ ልጽፍ ጀመርኩና ምን እንደምጽፍ ግራ ገባኝ። የምር …. ለኢሕአዴግ ምክር እንዳንጽፍ ኢሕአዴጎች የሚሰሙ አይመስሉም። አቶ ኃይለማሪያም ይቅርታ ጠየቁ፣ ምሁራንን አነጋገሩ የሚል ነገር ሰምተናል። ግን መሰረታዊ ፣ በሕዝብ ዘንድ መተማመን የሚፈጥር ፣ ተስፋን የሚጭር ነገር ሊኖር እንደሚችል የሚያመላክት ነገር አላየንም።ለምሳሌ እስረኖችን በሙሉ መፍታት፣ ካሉ ሕጋዊ ተቃዋሚዎች ጋር መወያየት የመሳሰሉት ….
በኢሕአዴጎች ላይ በግለሰብ ደረጃ ጥላቻ በጭራሽ የለኝም። “ጥሩና የሚጠቅም ነገር አደረጉ፣ ጥሩ መስመር ያዙ” የሚል ትንሽም ቢሆን አስተሳሰብ ዉስጤ ከገባ፣ ያንን ከማበረታታት ወደ ኋላ አልልም ። ግን አሁን ምንም ነገር የለም።
በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዙሪያ እንዳንጽፍ “ተባበሩ፣ ተሰባሰቡ” ብለን መከርን፣ የመፍትሄ ሐሳቦችን አቀረብን፣ ግን አልሰሙም። ሰማያዊ፣ መኢአድ፣ ኢዴፓ ፣ ትብብር፣ መድረክ፣ የቀድሞ አንድነት …አሁንም በተናጥል እየነጎዱ ነው። ሸንጎ፣ የሽግግር ምክር ቤቱ፣ ግንቦት ሰባት. ኦዴፍ፣ ሶሊዳሪቲ …ሁሉም አሁንም በተናጥል እየነጎዱ ነው። ስለዚህ በተቃዋሚዎች ፖለቲካ ዙሪያ ልንጽፍ የምንችለው ነገር የለንም። ተቃዋሚዎች ቢሰባሰቡ የነርሱ ደጋፊ ሆነን (አንድነት ፓርቲን እንደግፍ እንደነበረው) ድጋፍ እናደረግ ነበር። በተቃዋሚዎች ዘንድ ትንሽም ቢሆን የተለወጠ ነገር እና አስተዋጾ ልናበረክትበት የምንችለው ነገር ካለ የድርሻችንን ከማድረግ ወደ ኋላ አንልም። አሁን ግን ብዙ ብዙም ሥራ የሚሰራ ተቃዋሚ አለ ማለት አይቻልም።
ሁልጊዜ ብሶት ማሰማት ደግሞ አድካሚ ነው።የለዉጥ፣ የመፍትሄ፣ የመልካም አማራጭ ፖለቲካ እንጂ የብሶት፣ የዘረኝነት ፖለቲካ አሰልቺ ሆኗል።
ለማንኛው በሂደት የምናየው ይሆናል። ለፍትህ ለሰላም፣ ለዴሞክራሲ ለእርቅ መቆማችንን እንቀጥላለን። እኛ አሜሪካን ስላለን፣ የተመቻቸ ኑሮ ስለምንኖር ፣ ራስ ወዳድነትን መርጠን፣ ሌሎችን አንረሳም። ለተገፉት፣ ለተጨቆኑት፣ በደል ለሚፈጸምባቸው፣ በግፍ ለታሰሩት መጮሃችንን እንቀጥላለን። ዘረኝኘት ይወገድ ዘንድ ፍቅርና መቀባበል ፣ አንድነትና መቻቻልን መስበካችንን እንቀጥላለን። ከሁሉም እና ከምንም በላይ ደግሞ በገዢዎች፣ በተቃዋሚዎች፣ በሁላችንም ዘንድ የአስተሳሰብና የአመለካከት ለዉጥ ይመጣ ዘንድ ጸሎታችንን እንቀጥላለን። የአገር ትንሳኤ የሚመጣው ለዉጥ በ እያንዳንዲ ዜጋ ዘንድ ሲኖር ነው። ጤናማ አስተሳሰብ ያላቸው ዜጎች ሲበዙ፣ ጤናማ አስተሳሰቡ በመንግስትም ሆነ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዉስጥ ይንጸባረቃል። ኢሕአዴግም ሆነ ተቃዋሚዎች የኛ ዉጤት ናቸው።የሕብረተሰቡ ዉጤት ናቸው።