እነ በቀለ ገርባ ምርመራ አላለቀም በሚል ሰበብ ነው ተጨማሪ ቀን ተጠየቀባቸው።ጠበቃ ችሎት እንዳይገባ ተከልክሏል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


እነ በቀለ ገርባ ምርመራ አላለቀም በሚል ሰበብ ነው ተጨማሪ ቀን ተጠየቀባቸው።ጠበቃ ችሎት እንዳይገባ ተከልክሏል።
እነ በቀለ ገርባ እና ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ጉዳያቸው የሚታየው በዝግ ችሎት ቢሆንም ግቢ ውስጥ ግን በርካታ ሰዎች ተገኝተው ነበር። እንደተለመደው ለተጨማሪ 28 ቀን ተቀጥረዋል። ለሚያዚያ 7, 2008። በቀለ ገርባ፣ አዲሱ ቡላላ እና ደጀኔ ጣፋ ቃላቸውን ሰጥተው የጨረሱ እና የፈረሙ መሆናቸውን ጠቅሰው ተጨማሪ ቀጠሮ እንዳይጠየቅባቸው ቢጠይቁም፤ ምርመራ አላለቀም በሚል ሰበብ ነው ተጨማሪ ቀን የተጠየቀባቸው።ካሁን በፊት የነበቀለን ጉዳይ ይዞ ፍ/ቤት የሚቆምላቸው ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ዛሬ ውክልና የለህም ተብሎ ችሎት እንዳይገባ ተከልክሏል። ማእከላዊም ብዙ ጊዜ ቢመላለስም ሊያገናኙት አልፈቀዱም።አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የችሎቱን ሁኔታ ለመከታተል በአራዳ ፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር።

በቀለ ገርባ “መታሰር ምንም ማለት አይደለም። አስሮ ሰብዓዊ መብትን መጣስ ግን የትም ሃገር የሌለ ነው። እንደ ኢትዬጵያ መንግስት ጨካኝ የለም። 4 በ 5 በሆነች ቤት የምንኖረው 23 እስረኞች ሆነን ነው። እዛችው ቤት ውስጥ ለሽንት የምንጠቀምበት ባልዲ እና የሁላችንም ልብስ ይቀመጣል። ይህን ተቃውመን የረሃብ አድማ ብናደርግ ‘ከፈለጋችሁ መሞት ትችላላችሁ’ ነው የተባልነው። እኛም ለመሞት ዝግጁ ነን።” ሲል ለሚዲያዎች መልእክቱን አስተላልፏል::