የወያኔ የሃሰት ይቅርታ እስር አፈና እና ግድያን በኦሮሚያ መውለዱን ቀጥሏል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi's photo.

የወያኔ የሃሰት ይቅርታ እስር አፈና እና ግድያን በኦሮሚያ መውለዱን ቀጥሏል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎Wellega‬ ‪#‎Arsi‬ ‪#‎Harerge‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የፌዴራል ፖሊስን የለበሱ የወያኔ አግኣዚ ወታደሮች እና ቅጥረኞች በአርሲ ወለጋ እና ሃረርጌ በሰላማዊው ሕዝብ ላይ የግድያ የእስር እና አፈና ተግባራቸውን መፈጸም መቀጠላቸው ሲታወቅ ሕዝቡም በደል በቃኝ ግድያ ይቁም ወታደሮች ይውጡልን ሲል ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሏል::

Minilik Salsawi's photo.

በዛሬው እለት በወለጋ ነቀምት ከኒው ጄኔሬሽን ዩንቨርስቲ ስድስት ወንዶች እና አንዲት ሴት ተማሪዎች በፖሊሶች ከዩንቨርስቲው ታፍነው መወሰዳቸው ታውቋል::የወያኔው አሻንጉሊት ሃይለማርያም ደሳለኝ ለጊዜ መግዣ እና ለማደናገሪያ ይቅርታ የሚለውን ቃል ከተናገረ በኋላ ግድያው አፈናው እስሩ እና ድብደባው ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆችን በጥይት ማቁሰል በሕወሓት አግኣዚ ወታደሮች ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን ሰላማዊውን ሕዝብ መውጫ መግቢያ አሳጥተውታል::ይህ በፎቶ ላይ የምትመለከቱት በአርሲ የሙኒሳ ወረዳ ነዋሪ ታዳጊ ሃጂ ብዙነህ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በአግኣዚ ጥይት ቆስሎ በአሰላ ሆስፒታል በመታከም ላይ ይገኛል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬