አለም ነቅቷል ማጭበርበር ይብቃ !!! ከ20 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተርቦ በምግብ እህል ራሳችንን ችለናል???


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አለም ነቅቷል ማጭበርበር ይብቃ !!! ከ20 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተርቦ በምግብ እህል ራሳችንን ችለናል???
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthiopiaEconomy‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Bloomberg‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Change‬

Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – አይኑን በጨው ያጠበው ወያኔ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ለመርጨት እና የራሱን ስም ለማቆለጳጰስ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለጋዜጠኞች ለዲፕሎማቶች እና ሚዲያ ደላሎች ጉቦ እንደሚሰጥ እና ለሎቢ እንደሚያውል በተግባር የተረጋገጠ ጉዳይ ነው::20 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በተራበበት አገር በምግብ እህል ራሳችንን ችለናል ይሉናል::የሃገሪቱ ኢኮኖሚ 11% አድጓል ይሉናል በየአመቱ አስረአንድ በመቶ አድጓል ማለት ምን ማለት ይሆን ? አላልንም 8 ከምናም ነው ያደገው ብለው ያለፉትን አመታት የቁጥር ቁልልንም እነ አይኔን ግንባር ያድርገው ይክዳሉ::

Minilik Salsawi's photo.

እንደ ቻይና ያሉ የአለምን ገበያ የተቆጣጠሩ ሃገሮች እንኳን 9 ከመቶ ላይ ለመድረስ እየተፍጨረጨሩ ባሉበት በዚህ ዘመን ላይ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በብድር የተያዙ ሕዝቦች በረሃብ በስራ አጥነት እና በስደት እየተንገላቱ የአገልግሎት አቅርቦት ባሌለበት የመልካም አስተዳደር አፈር በበላበት ፍትህ በተቀበረበት ጥቂቶች በገነኑበት ባለስልጣናት የተደራጀ የወሮበላ ቡድን በሚመሩበት ሙስና በተንሰራፋበት በገሃድ በሚዘረፍበት አገር እንዴት 11% ይታደጋል:: ውሸት ሲደራረም ውነት ይሆናል የሚሉት ያለፈበት የሞኝ ብሂል ወያኔ ያዋጣኛል ብሎ እየተንዘፈዘፈበት ይገኛል::

አምስት ከመቶ እድገት ለማግኘት ገና 20 አመት መስራት ይጠበቃል በተባለላት ኢትዮጵያ አርከበ እቁባይ የተባለው የወያኔ ባለስልጣን ለብሎምበርግ በሰጠው ቃለመጠይቅ ላይ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ አድጎ ጨረቃን መንካቱን ለፈፈ::የወያኔ ባለስልጣናት ኪሳቸው ሲሞላ የሕዝብ ኪስ የሞላ የሚመስላቸው…የሚጠጣው ውሃ ጥቶ ጀሪካን ያሰለፈ ሕዝብ ሳይታያቸው የተጣራ ውሃና ውስኪ ስለጠጡ ብቻ ሕዝብ ሁሉ የጠጣ የሚመስላቸው …በመንግስት ገንዘብ የገዙትን ጄኔሬተር እየተጠቀሙ እነሱ በብርሃን ስለሚመላለሱ ሕዝብ ሁሉ ባለ መብራት የሚመስላቸው … ጉዳቸው የማያልቅ ወያኔዎች እነሱ እና ዘመዶቻቸው ስላደጉ ብቻ ሕዝብ በድህነት እየተንቆራፈደ የለውጥ ያለ ሲል የማይገባቸው ደነዞች መወገጃቸው ጊዜ ደርሷል::ኢትዮጵያውያንም ነቅተናል !!!ነጮቹም ነቅተዋል !!! ትግሉ ይቀጥላል!!! ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው!!! ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬