በኢትዮጵያ የተከሰተው ርሀብ በከፋ የምግብ እጥረት የሚጎዱ ሰዎች ቁጥር በአለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው 15 በመቶ በላይ መድረሱ እንዳሳሰበው የአለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከሃምሳ አመት ወዲህ የተከሰተ ከፍተኛ ርሀብ ነው የተባለው በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የርሀብ አደጋ በከፋ የምግብ እጥረት የሚጎዱ ሰዎች ቁጥር በአለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው 15 በመቶ በላይ መድረሱ እንዳሳሰበው የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) አስታወቀ።
ርሀቡ እያደረሰ ያለው ጉዳት በአለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው መጠን በላይ መሆኑንም ለእርዳታ ተቋማት እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የአለም ምግብ ፕሮግራም ቃል አቀባል ቻሊስ ምክዶኑግ አስረድተዋል። በርካታ አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለውን የድርቅ አደጋ ከአንድ ወር በኃላ ወደ ረሃብ ሊለወጥ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ ድርቁ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ከተጠበቀው በላይ ከፍተኛ መሆኑን ዩኤስ ቱደይ ጋዜጣ ዘግቧል።
በሰሜን፣ መካከለኛ እና ምስራቅ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ቦታዎች ረሀብ አፍጥጦ እየመጣ ነው፡፡ ከአምስት ሳምንት በኋላ እዚህ ቦታ ምንም የሚበላ ምግብ ላይኖር አንደሚችል አለም አቀፈ የረዲኤት ድርጅቶች ገለጸዋል፡፡ ሚያዝያ ሲመጣ በ10 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ምንም የሚበላ የሚቀመስ እንደማይኖራቸው ተናግሯል፡፡ በሌላ በኩል የህወሀት መራሹ ባለስልጣን ለእርዳታ እየገቡ ያሉትን እህሎች ጅቡቲ ወደብ ላይ እያለ ለራሳቸው ጥቅም ሸጠው እያዋሉት መሆኑን በሀገር ቤት ያለ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ርሀቡን ለመቋቋም አለም አቀፍ የረዲኤት ድርጅቶ 1.4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ በተደጋጋሚ እያሳሰቡ ይገኛል፡፡ እስካሁን ድረስም ከአለምአቀፍ ለጋሽ ሀገራት የተገኘው ገንዘብ በጣም ትንሽ እንደሆነም የተ.መ.ድ ገልጿል፡፡

Nigussie Woldg's photo.
BBN NEWS