የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር – ዶይቸ ቬለ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በተለያዩ ምክንያቶች ከአፍንጫ ደም ሊፈስ ይችላል። ነስር የምንለዉ ማለት ነዉ። ብዙዎች መንስኤዉ ምንድነዉ ብለዉ ይጨነቃሉ። ነስር ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የመሆኑን ያህል አብዛኛዉን ጊዜ ቤት ዉስጥ ሊቆጣጠሩት የሚቻል እንደሆነ አንዳንድ የህክምና ጽሑፎች ይጠቁማሉ። ሆኖም አልፎ አልፎ ደግሞ ብዙ ደም የሚፈስበት ከባድ ነስር ሲያጋጥም የሀኪም ርዳታ ማግኘት አማራጭ እንደማይኖረዉም ያሳስባሉ። የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር መንስኤዉ አንድ ብቻ አይደለም፤ የተለያዩ ህመሞች እና ምክንያቶች ሊያመጡት እንደሚችሉ ዶክተር ቶሌራ ወልደየስ የዉስጥ ደዌ ከፍተኛ ሃኪም አስረድተዋል።
መንስኤዎቹ የሚጣሩት ችግሩ ያጋጠመዉ ግለሰብ ሃኪም ጋር ቀርቦ በሚደረግ ምርመራ እና ማብራሪያ አማካኝነት ነዉ። እንደሃኪሙ ከሆነ ነስሩ ከፍተኛ ሲሆን ብቻ አይደለም ወደሃኪም መሄድ የሚገባዉ። የሚነስረዉ ሰዉ መንስኤዉን ለማወቅ ከአንገት በላይ ህክምና ባለሙያ ዘንድ ሄዶ በምን ምክንያት ያ እንደተከሰተ መመርመር ይኖርበታል። ነስር በሽታ ነዉ? አንድ ሰዉ ሲነስረዉ በመጀመሪያስ ምን ማድረግ ይኖርበታል? የሃኪሙን ማብራሪያ እና ምክር ለመከታተል የድምጽ ዘገባዉን ይጫኑ → listen