ብሄራዊ መግባባት የሚፈጠረው ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ሲኖር እንጂ ምሁራንን ሰብስቦ በመጮህ አይደለም::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ብሄራዊ መግባባት የሚፈጠረው ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ሲኖር እንጂ ምሁራንን ሰብስቦ በመጮህ አይደለም::
#Ethiopia #EPRDF #EthiopianOppositionparties #Ethiopiaprotests #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – አዲሱ የጊዜ መግዣ ዲስኩር – ብሄራዊ መግባባት መፍጠር – ወያኔ ሕዝብን ማታለል ልማዱ ስራው ተግባሩ አድርጎ ይዞታል::ወያኔ ምሁራንን ሲያወያይ ይህ ለመጀመሪያው አይደለም አዲስ አበባን በገበሬውና በኤምፔሪያሊዝም ድጋፍ ሲቆጣጠር ጀምሮ ምሁራን ሲያወያይይ ካለንበት የተበላሸ ፖለቲካ ላይ ደርሷል::ሁልግዝጥ እቅድ ነድፈናል ከማለት ውጪ አንድም ጠብ ያለ የተሻሻለ ነገር የለም::ዜጎች በአገራቸው ጉዳይ እንዳይሳተፉ እንዲሳቀቁ እንዲደነብሩ ወዘተ ከግድያ ጀምሮ እስከ እስር እና ማሳደድ ድረስ በፊት ለፊት ካለእፍረት ተግብሯል::ሕዝብ መንቃቱን እንኳን አንድም የማይባንነው ወያኔ ሁል ግዜ ማዘናጊያ እና ጊዜ መግዣ ብሎ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ያለፈባቸው እና ችግሮችን ከማባባስ ውጪ ምንም የፈየዱት ነገር የለም::ባለንበት 21ኛ ክፍለ ዘመን ፖለቲካው በስሏል አገራት ዜጎቻቸውን መወንጀል ትተው ኢኮኖሚያቸውን ሲገነቡ እያየን ነው::እንናገረው ብንል ብዙ ማለት ይቻላል ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ በፍጹም የለም::ግልጽነት እና ተጠያቂነት ስላሌለ አገሪቷ የመሃይማን እና የሌቦች መፈንጫ ሆናለች::
ወያኔ ተናግሮ እንደማይጠግበው እንደደርግ ሃገር ሊለውጡ የሚችሉ እና ተስፋ የሆኑ የተማሩ ወጣት ትውልዶችን በጠራራ ጸሃይ እየደፋ ይገኛል::የወያኔ ወንጀሎች ተነግረው አያልቁም አሁን ዋናው አትኩሮት ወንጀል እና ወንጀለኞችን ማስወገድ ያስፈልጋል የሚለው ጊዜ ላይ ደርሰናል::ወያኔ ከአገዛዝ ሂደቱ በጎሳ ፖለቲካ ከፋፍሎ መግዛት እንዳልተሳካለት እያየው ነው::በፕሮፓጋንዳ እና በሃሰት መግዛትም ሕዝቡን እንዳስመረረው እያየው ነው::ራሱም ወያኔ በራሱ ላይ መስክሯል::ታዲያ ም እየተጠበቀ ነው ማስተዳደር መምራት ካልተቻለ ስልጣን መልቀቅ አንድ እና ብቸኛ መፍትሄ ነው::መርጦኛል ያለው ሕዝብ አልመረጥኩህም ብሎ እስከ ሕይወት መስዋትነት ከፍሎ በተግባር ወያኔን እንደማይፈልገው አሳይቷል::ዝም ያለውም ሕዝብ ለውጥ ፈላጊ እደሆነ መዘንጋት የለብንም::ዝምታ በራሱ ከባድ እና አደገኛ ተቃውሞ ነው::
የሃገሪቱን ችግር ለመፍታት በሚል በሁለት በኩል የተሳለው የወያኔ ምላስ ሕዝብን ለማጭበርበር እና ጊዜ ለመግዛት የማይቧጥጠው ነገር የለም::ከዚህም አንዱ የሃስት ይቅርታውን ተከትሎ ምሁራን ከሚላቸው ጋር ስብሰባ መቀመጡ አንደናው የማዘናጊያ መገድ ነው:;የወያኔ አገዛዝ የምሁራንን ምክር ቢሰማ ኖሮ አሁን የምናያቸው ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ባልተፈጠር ግድያዎች እና እስሮች እንዲሁም ሕዝብ ማፈናቀል ማሳደድ እና መዝረፍ ሙሰኝነት በሃግሪቱ ልቀው አይገኙም ነበር::ወያኔ ካሁን በኋላ ጊዜው አልፎበታል::ያለው እድል ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ ብቻ ነው:; ዘረፋ እና የሕዝብ ደም መጠጣት የለመዱ የወያኔ ባለስልጣናት ሰይጣናዊ ባህሪያቸውን ይቀይራሉ ማለት አንድም የዋህነት ሌላም ሞኝነት ነው::ስለዚህ ይሃገሪቱ ችግሮች ብቸኛው አማራጭ ወያኔን አውርዶ ሕዝባዊ መንግስት መመስረት ብቻ ነው::ብሄራዊ መግባባት የሚፈጠረው ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ሲኖር እንጂ ምሁራንን ሰብስቦ በመጮህ አይደለም::ጊዜ መግዣ አጀንዳ !#ምንሊክሳልሳዊ
