ፀሓይ እና ጨለማ የተፈራረቀባት ከተማ = ዓድዋ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ፀሓይ እና ጨለማ የተፈራረቀባት ከተማ ዓድዋ ……..
የታሪክ ባለቤት፣ የትሪዙም መስህብ፣ የንግድ ማዕከል፣ የቅዱሳን ማረፈያ፣ ወደ ሳይንስ ዓለም ቀድመው ከተቀላቀሉ በግንባር ቀደም የምትጠራ ፣በኃይማት መቻቻል እና አብሮ በመኖር የምትታወቅ፣ ተስአቱ ቅዱሳን 450 ዓ/ም አካባቢ ከሮማ ተሰደዎ የተጠለሉባት፣ የሴም እና ኩሽ ቃል ኪዳን የገቡባት ምድር፣ ከሀ ይቀድማል ይሓ ባለቤት፣ የመጀመርያ የአክሱም ስልጣኔ እንዳ ፅዮን ግቢ የንግድ ማዕከል፣ የሃፀይ የውሃንስ የመጀመርያ ቤተ መንግስት ልዩ ስሙ ደብርቺ ደብረ ብርሃን ባለቤት፣ የአንድነታችን ምልክት ፣በአፀይ ሚኒሊክ መሪነት በእነ አሉላ ፣ጣይቱ ፊታውራሪነት የአፍሪካውያን ድል ለአለም የተመሰከረበት፣ አባቶቻችን ቀና ብለው አፍሪካውያን ቀና ያደረጉበት፣ 1888 የአባቶቻችን ድል ባቤት ዓድዋ፣ በንጉስ ሃይለ ስላሴ ከተገነቡ የመጀመርያዎቹ ት/ትቤቶች ንግስተ ሳባ ትምህርት ቤት ባለቤት፣ ደርግን ለመጣል ከተደረገ አድካሚ ጉዞ ኣብራ የተጎዘች የለውጥ ፈር ቀዳጅ ልጆችዎ አስተምራ መርቃ ወደ ትግል የላከች ዓድዋ፣ ከውድቀት ደርግ በኃላ አይደደለም እስከ ኑጉስ ኃይለ ስላሴ የነበራት ፈርቀዳጅነት፣ መሪነት ይዛ መቀጠል ይቅርና የነበረው ታሪክ፣ማንነት፣ልማት ወደ ኋላ እየተመለሰ፣ እየተመለሰ፣እየተመለሰ ጫፍ ደረስዋል፡፡

መልካም አስተዳደር ፣ ፍትሕ፣ ልማት የለም ብለን ብንፅፍ ማጋነን አይሆንም እንደ ሃወልት የቆሙ ጅምር ህንፃዎች ማየት የተለመደ ነው፤ በንግድ የተሰማሩ ባለሃብቶች የተመቻቸ አሰራር በለመኖሩ ፣ ያለ አግባብ ግብር ክፈሉ በመባላቸው ዓድዋን ትተው ተሰደዋል፤ ብዙ ወጣት የተወለደበት፣ ያደገበት ዓድዋን ትቶ ከመሃል ሀገር እስከ ዓረብ ሀገራት ወደ ስደት አምርተዋል፣ ፈልሰዋል ማለት ይቻላል፡፡የመጀመርያ የህወሓትን ዱላ የቀመሰች ዓድዋ ብየ ስፅፍ ማጋነን አይሆነብኝም፡፡

ማን ነው እንዲህ የሚያደርግ? ስለ ምን እንዲህ ይደረጋል? በማለት የተለያዩ መላ ምቶች የሚፅፉ አሉ፡፡እውነታው ግን ማን? ለምን? የሚሉ የዓድዋ በደሎችን ለመመለስ ዓድዋ ተወልዶ ማደግ በቂ ይመስለኛል፡፡ይነገረን ካላቹ ግን እስኪ ነስራቹ ልንነግራቹ እንችላለን፡፡ግን ትርፉ ብስጭት ነው እና ይቅርብን ይቅርባቹ፡፡

በዓድዋ ይሰራሉ ከተባሉ ፕሮጀክቶች መሃል ያልተሰሩ ቁጥር ከመቁጠር፡፡ ድሮ የተሰሩ ግን የፈራረሱ መቁጠር ይቀላል፡፡ሁሌ ውሸት ሁሌ ፕሮፖጋንዳ ከመሰራት ማፈረስ ይቀላቸወል፡፡ ስለ ዓድዋ ስፅፍ አንድ አንዴ ስሜታዊ እሆናለው…..ምክንያቱም ዓድዋን የማውቃት በወግ፣በመጣጥፋ ሳይሆን በእውነታው ዓለም ነው በእውነታው ዓለም ሁነህ የጎሰቆለች ዓድዋን ማየት ፀሓይ እና ጨለማ የጠፈረረቀባት ዓድዋ ማየት ያሳምማል…..

እስኪ ይሁን በማለት ጨለማ ለማጥፋት የሚታገል ብርሃን በፅንስ ሃሳብ ደረጃ ሸተተኝ እና ወደዛ ልመልሳቹ …..

በቅርቡ ዓድዋን በተመለከተ ፓን አፍሪካኒዝም ዩኒቨርስቲ አፍሪካውያን ሪሰርቻቸው እየመጡ የሚሰሩበት ትልቅ የአፍሪካውያን አህጉራዊ ዩኒቨርስቲ ለመገንባት ፕሮጀክትን በመቅረፅ እንቅስቃሴ የጀመሩ እነ ፕሮፌሰረ እንድርያስ ፕሮፌሰር ክንፈ አቶ ቢተው በላይ የመሳሰሉ ግለ ሰዎች ከልብ ላመሰገን እወዳለው እውነት ይህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሁኖ እንየው ይሁን? ወይስ ይህ እንደለመድነው የውሃ ሽታ ሁኖ ይቀራል? ይህንን ፕሮጀክት እውን እንዲሆን የበኩላችን ተራ እንጫወት ልለያ ፅሑፌ አላለቀም ይቀጥላል፡፡

ፀሓይ እና ጨለማ የተፈራረቀባት ከተማ
ዓድዋ

Kinfegebrail Gyohans's photo.
Kinfegebrail Gyohans's photo.