አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጂ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደን አስመልክቶ መግለጫ አወጣ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ድርጅት ሲፒጄ በቅርቡ በችሎት ላይ ሶስት አመት ከአስራ ወር ከተበየነበት በሁላ በሁላም ከችሎት በሁላ በንባብ ስህተት ነው በሚል አራት አመት ከአስር ወር የተፈረደበትን ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደን አስመልክቶ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል

በኢትዮጵያ ከ2013 ጀምሮ የታሰረው ጋዜጠኛ የእስር ቅጣት ተበየነበት

ኒውዮርክ፤ ማርች 11/2016 – አሁን በሕትመት ላይ የማትገኘው የ‹‹ሙስሊሞች ጉዳይ›› መጽሔት ሥራ አስኪያጅ የነበረው ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ በጸረ ሽብር ሕጉ ተከስሶ ከታሰረ ከሦስት ዓመታት በኋላ የእስር ቅጣት ተበየነበት፡፡ የተፈረደበትን የእስር ቅጣት ርዝመት አስመልክቶ የተለያየ ዘገባ የደረሰው ሲጂጄ ለጊዜው ትክክለኛውን ፍርድ ለማጣራት አልቻለም፡፡

‹‹በጃንዋሪ 2013 ከታሠረ ወዲህ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ሙያዊ ኃላፊነቱን በመወጣቱ ብቻ ለከፍተኛ የስቃይ ቅጣት ተዳርጓል›› ያሉት የሲፒጄ ምክትል ኤክሲኪውቲቭ ዳይሬክተር ሮበርት ማሆኒ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሉን አላግባብ በመጠቀም በጸረ ሽብር ሕጉ አማካኝነት ወቃሽ (ሐያሲ) ድምጾች ላይ የሚፈጽመውን ጥቃት ሊያቆም ይገባል›› ሲሉ አክለዋል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ፕሮጀክት›› የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በትዊተር ገጹ በዛሬው እለት እንደዘገበው ከሆነ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ላይ የተላለፈው የእስር ቅጣት 3 ዓመት ከ11 ወር ቢሆንም ችግር እንዳይደርስባቸው በመሥጋት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሁለት ጋዜጠኞች የተላለፈበት ቅጣት 4 ዓመት ከ10 ወር መሆኑን እና እስካሁን የታሰረበት ጊዜም በዚሁ ቅጣት ውስጥ እንደሚካተትለት ለሲፒጄ ገልጸዋል፡፡ ሲፒጄ እስካሁን ትክክለኛውን የቅጣት መጠን ለማጣራት አልቻለም፡፡ የሲፒጄ ዓመታዊ የወህኒ ቆጠራ እስከወጣበት ዲሴምበር 1 ድረስ ኢትዮጵያ በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ሁለተኛ የነበረች መሆኑ ይታወሳል፡፡

Abdurehim Ahmed's photo.