የድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ “ሽረት”ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በታዋቂው ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ተደርሶ፣ዳይሬክት የተደረገው “ሽረት” ፊልም መጋቢት 24 በብሔራዊ ቲያትር እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡ የ1 ሰዓትከ30 ደቂቃ ርዝማኔ ባለው በዚህ ፊልም ላይ ራሱአቤል ሙሉጌታ፣ ሰላማዊት አስማማው፣ መቅደስ ባዬና ዮናስ አሰፋን ጨምሮ በርካታ ተዋናዮች የተሳተፉበት ሲሆን ፊልሙ ልብ አንጠልጣይ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ፊልሙን ለመስራት ከ750ሺህ ብር በላይ እንደፈጀበት የገለፀው ድምፃዊው፤ ከድርሰቱ አንስቶ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 4 አመታትን ፈጅቶብኛል ብሏል፡፡ የፊልሙ ጭብጥ በፍቅርና በቀል ዙሪያ ያጠነጥናል ተብሏል፡፡ ወደፊልም ያስገባኝ የፊልሙን ኢንዱስትሪ ለማሳደግ ያለኝ ቁጭት ነው ያለው ድምፃዊው፤ “ለአንድ አመት ዳይሬክቲንግ ተምሬ፣ የነበረኝንም እውቀቶች አዳብሬ ምርጥ የምለውን ፊልም ሰርቻለሁ ብሏል፡፡
አርቲስቱ በብዙ መልኩ ፊልሙ ላይ የተሳተፉበትን ምክንያት ሲናገርም “አንድ ሰው በአራትም በአምስትም ነገሮች ላይ የተካነ ሊሆን ይችላል፤ ዋናው ነገር በዳይሬክቲንጉም በድርሰቱም በሌላውም መሳተፍ ሳይሆን በጥራት መስራቱ ነው፤ እኔ ደግሞ እችላለሁ ብዬ ስላመንኩ ሰርቻለሁ፡፡ይህንንም አይታችሁ መስክሩ” ሲል ተናግሯል፡፡ ከመንፈሳዊ ህይወት ጋር በተገናኘ ከሙዚቃ ሙያ ወጥቷል እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የገለፀው አርቲስቱ፤ “ለፊልም ስራውብዬ ከአመት በላይ ከሙዚቃው ርቄ ብቆይም ቀጣይስራዬ የሚሆነው 3ኛ አልበሜን ለመጨረስ መሯሯጥነው” ብሏል፡፡ Addis Admass