በ13 ዓመቷ ለተደፈረችው ታዳጊ መንግሥት 150 ሺ ዶላር እንዲከፍል ተወሰነበት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


መቀመጫውን በጋምቢያ ያደረገው የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ፍ/ቤት፤ በ13 አመቷ ለተደፈረች ኢትዮጵያዊት ታዳጊ መንግስት ተገቢውን ፍትህ እንድታገኝ አላደረገም በሚል የ150ሺህ ዶላር የሞራል ካሳ ለተጎጂዋ እንዲከፍል መወሰኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከ13 ዓመት በፊት የተደፈረችው ታዳጊዋ፤ በወቅቱ ለፍ/ቤት ተደፍሬያለሁ ብላ አቤት ብትልም ፍ/ቤቱ ከመደፈሯ በፊት ድንግል ለመሆኗ ማስረጃ እንድታቀርብ ጠይቋት ባለማቅረቧ፤ “ድንግል የሆነች ሴት ብቻ ነች ተደፈረች የሚባለው” በማለት ክሷን ውድቅ አድርጐባት ነበር ብሏል – ቢቢሲ፡፡
ውሳኔው ከተሰጠ ከ4 ዓመት በኋላ የመብት ተሟጋቾች ጉዳዩን ወደ አፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን መውሰዳቸውንና ተቀማጭነቱን በጋምቢያ ያደረገው የኮሚሽኑ ፍ/ቤት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የታዳጊዋን መብት አለማስከበሩንና የሴቶችን እኩልነት አለማረጋገጡን በማመልከት፣ ለታዳጊዋ የሞራል ካሳ እንዲሆናት መንግስት 150ሺ ዶላር (ከ3 ሚ.ብር በላይ) እንዲከፍላት ወስኗል፡፡
ታዳጊዋ በደፋሪዋ ተጠልፋ እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው፤ በወቅቱ ጋብቻ የፈፀመችው ተስማምታ ነው ቢባልም በጋብቻ ወረቀቱ ላይ ተገድዳ ለመፈረሟ ማረጋገጫ መገኘቱን ፍ/ቤቱ ጠቁሞ፤ “ታዳጊዋ ተስማምታ ሳይሆን ተገዳ ተደፍራለች” ብሏል፡፡
“ድንግል የሆነች ሴት ብቻ ነች ተደፈረች የሚባለው” በሚል በዋስ ተለቆ የነበረው ጥቃት ፈፃሚው፤ ዋስትናው ተነስቶ በድጋሚ ለ10 ዓመት ታስሮ የተለቀቀ ሲሆን ዓለምአቀፍ የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ዘገባው፤ “ኢትዮጵያ የወሲብ ጥቃት ለሚደርስባቸው ሴቶች በቂ ጥበቃ የሚያደርግ ህግ የላትም” ሲሉ ትችታቸውን ሰንዝረዋል፡፡
በአሁን ወቅት ተጐጂዋ በ20ዎቹ እድሜ አጋማሽ ላይ እንደምትገኝ ዘገባው ጠቅሶ ሰላማዊ ህይወት እየመራችና ትምህርቷንም እየተማረች እንደሆነ ጠቁሟል፡፡