የሳምንቱ አጀንዳ — ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ክልል – ብልጦች አይደለም ብልጣ ብልጦች ግን አይሸውዱንም::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የሳምንቱ አጀንዳ — ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ክልል – ብልጦች አይደለም ብልጣ ብልጦች ግን አይሸውዱንም::
#Ethiopia #Amhara #Tigray #TPLF #ANDM #ገዱ_አንዳርጋቸው #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – አጣብቂኙ አላላውስ ሲለው ሕወሓት አጀንዳ ፈጠራ እና ማምታታቱን ማዘናጋቱን ተክኖበታል::ሕዝቡ ለእለት ኑሮው ስለሚጣደፍ የተባለውን ይሰማል ያፈሳል የምትለው ሕወሓት በአማራ ክልል ዙሪያ ለገባበት አጣብቂኝ እና መስራት ለሚፈልገው ስራ ገዱ አንዳርጋቸውን እንደ አጀንዳ ይዞ መጥቶ የማህበራዊ ድረገጽን እስት እያራገበበት ነው::
አያሌው ጎበዜ ሲወርድ ለሱዳን መሬት ቆርሼ አልሰጥም አልፈርምም ስላለ ነው ተባለ ተራገበ አያሌው ኢስታንቡል ላይ ተቀምጦ የተባለውን ተቃራኒ ተናግሮ አራጋቢዎቹን አሳፈረ ገዱ ወደ ስልጣን ሲመጣ የወያኔ አለቅላቂ ስለሆነ ተባለ ዛሬ ላይ ደሞ ለወያኔ የማዘናጊያ ስልት መጠቀሚያ ሲሆን አብረው የሚያጨበጭቡ ዝግምተኛ ዝንጉዎች ተፈጥረው የነበሩትም ሳይሻሻሉ ማየት እጅግ ይሳፍራል:;ገዱም ሲተካካ ተርቱለት…ካለፈው መማር የማንችል የራሳችን ጠላቶች ሆነን እስከመች???
ሀገሪቱ ለውጥ ለውጥ ትሸታለች ከትልቅ እስከ ትንሽ ለውጥ ይፈልጋል የወያኔ የፖለቲካ እና የኢኮኦሚ ዱላ አንገብግቦታል::ሁሉም ስርኣቱ እንዲለውጥ ይመክራል ይዘክራል ይጸልያል ይቃወማል አደባባይ ወጥቶ ደሙን እስከማፍሰስ እስከመሞት ደርሷል::ወያኔ እና ግብረአበሮቿ ክበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊናበቡ አልቻሉም ፍትህ የለም ሰላም የለም ስራ የለም ኢኮኖሚው በአንድ ብሄር ስር ለማድረግ ሩጫው ተይዟል::የሃገር እና የውጪው የትምህርት እድል ለአንድ ብሄር ነው ስደት ተመራጭ ሆኗል ወዘተ ይህ ሁላ ባለበት አገር ላይ ሕዝቡ ለለውጥ እየታገለ አየሩም ለውጥ ለውጥ እየሸተተ ይገኛል::ይህ ደሞ ወያኔን አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተታት ማዘናጊያ መደፍጠጫ ስልቶችን ሁሉ እየቧጠጠች ትገኛለች::የአማራው ሕዝብ ነጻ የሚወጣው አለቅላቂ እና አራጋቢ ባልሆኑ ሃቀኛ ልጆቹ ነው::
የሳምንቱ አጀንዳ ደጉ አንዳርጋቸው ከአማራ ክልል … ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠ መሬት የለም ሊኖርም አይችልም ፤ የልጆች ጨዋታ አይደለም መሬትን አንስቶና ቆርሶ መስጠት አይቻልም ፡፡ … የቅማንትን የማንነት ጥያቄ አስታከው አካባቢውን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ የሚሯሯጡ ሃይሎች ከውስጥም ከውጭም አሉ ፤ እነርሱን በቃችሁ ልንላቸው ይገባል ፡፡ … የሚል በሳል ፣ ንቁ ፣ የሕዝብ ወገንተኝነት ያለው መሪ ማለት እርሱ ነው ፡፡ አሁንም በድጋሚ እጅ እንነሳለን የተከበሩ ….ዶሮን ሲያታልሏት …. ለማያቁሽ ሂጂና ታጠኝ አዳሜ .. ከጨዋታው በፊት በቂ መረጃ አለን አቦ ጭብርብር ካድሬዎች ተምታተው ሊያምታቱ ይፈልጋሉ::ብልጦች አይደለም ብልጣ ብልጦች ግን አይሸውዱንም::ማዘንጊያሽ … ሽሽሽሽሽሽሽሽ #ምንሊክሳልሳዊ
