ታደሰ ሲሳይ ሥልጣነ ክህነቱን ከተገፈፈ ሁለት ዓመታት ተቆጠሩ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአሌክሳንደሪያ፣ ቨርጂኒያ ሐመረኖህ ኪዳነ ምሕረት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን እንደ ግል ንብረቱ በመያዝ በዕብሪት አብጦ ያሻውን የሚያደርገው ታደሰ ሲሳይ ሥልጣነ ክህነቱን ከተገፈፈና ከተወገዘ ሁለት ዓመታት እንዳለፉት የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ይህ ግለሰብ የፈጸመው ዝሙት በማስረጃ ስለተረጋገጠ ከሁለት ዓመታት በፊት ሥልጣነ ክህነቱን የተገፈፈ ቢሆንም አሁንም ከአውደ ምህረት ላይ አልወርድም ብሎ ሙጭጭ ብሎ ይገኛል። ግለሰቡ ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቀኖና ውጭ በግል ስሙ እንደ ንግድ ተቋም አስመዝግቦ በያዘየው ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያፍሰውን ገንዘብ ካለምንም ተአቅቦና ይሉኝታ የዝሙት ጥማቱን እየተወጣበት እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ። ታደሰ ከጥፋቱ እንዲመለስና ንስሐ እንዲገባ የቀረበለትን ጥሪና መማጸን ከምንም ባለመቁጠር በአሜሪካን አገር ውስጥ ያለውን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችን በፓስተሮች ብቸኛ ቁጥጥር የመምራት አሰራር በሐመረኖህ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ውስጥ በማምጣት እራሱን የማይጠየቅና የማይወቅስ ንጉስ አድርጎ ሾሟል።

1234

ሥልጣነ ክህነቱ ተገፎ በንቀትና በእብሪት ቤተክርስቲያንን እያረከሰ የሚገኘው ታደሰ ሲሳይ ይህ ነው። አሁን ደግሞ መንኩሻለሁ እያለ ነው።

በተለይም አንዲት ባለትዳርና የልጆች እናትን በውሽማነት በመያዝ እጅግ አስከፊና አሳዛኝ ከአንድ ካህን የማይጠበቅ ዝሙት መፈጸሙን የሴትየዋ የቀድሞ ህጋዊ ባለቤት የነበሩት ሰው ባቀረቡት ማስረጃ አረጋግጠዋል። ከዚህም በተጨማሪም እንደ ሰፈር ተልከስካሽ ውሻ በፍትወት ስካር ያበደው ታደሰ ሲሳይ ከሌሎችም ሴቶች ጋር ዝሙት እንደሚፈጽም ነቀፋዎችና ትችቶች በተለያየ ጊዜ ሲቀርብበት ቆይቷል።ሆኖም ሰውየው በተደጋጋሚ ተመክሮ ሊመለስና ንስሃ ሊገባ ባለመፈለጉ ምክንያት እንደተወገዘ ይታወሳል። አንዳንድ ሰዎች ሲያወሩ እንደተደመጡት ሰውየው አሜሪካን ከመምጣቱ በፊት ጭራሹን ካህን አልነበረም፣ እንደውም ወያኔ የኢትዮጵያን ሰራዊት ከመበተኑ በፊት በውትድርና አገልግሎት ላይ የነበረና መጠሪያ ስሙ “ሲሳይ ታደሰ” እንደነበረና አሜሪካ ሲመጣ አዘዋውሮ “ታደሰ ሲሳይ” በማለት መጠራት እንደጀመረ ይናገራሉ።

በአቶ ታደሰ ሲሳይ ላይ ከሁለት ዓመታት በፊት ውግዘቱን ያወጁት ካህናት የካንሳስ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ፣የዋሽንግተን ዲሲ ርዕሰ አድባራት ደብረሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ሊቀ ማዕምራን ቀሲስ ዶ/ር አማረ ካሳዬና የቨርጂኒያ የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ቆሞስ አባ ኃይለ ሚካኤል ተከለኃይማኖት ናቸው። የውግዘቱ ሥነ ሥርዓት የተካሄደው በሕዝብ ፊት ሲሆን ይህንኑ ጉዳይ እንዲከታተል ከዚህ በፊት የተቋቋመው ኮሚቴ አባላትና ከተለየዩ አድባራት የመጡ ምዕመናንም ተገኝተው የነበረ መሆኑአይዘነጋም።

አቶ ታደሰ ሲሳይ የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. (ማርች 9, 2014) ስልጣነ ክህነቱ የተሰረዘና ወደ ተራ ምዕመንነት የወረደ መሆኑ ቢገለጽም በማን አለብኝነትና በዕብሪት አሁንም ቤተክርስቲያንን ማርከሱን ቀጥሎበታል። ታደሰ ሲሳይ እንደግል ንብረቱ የፈለገውን የሚያደርግባት የቨርጂኒያ ሐመረኖህ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ውስጥ ከምዕመናን የሚመነትፈውን ገንዘብ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ በመርጨት ጉቦ ከፍሎ በገዛው የምንኩስና ማዕረግ አሁንም ውንብድናውን ሳያፍርና ሳይሸማቀቅ ቀጥሎበታል።ይህንን ለትውልድ ሲያስጠይቅ የሚኖር በቤተክርስቲያንና በምዕመናን ላይ የተሰራ ወንጀል ኢትዮጵያ ድረስ ሰንሰለት በመዘርጋት በግምባር ቀደምትነት ተባባሪ የሆኑት በቀላማጅነታቸውና በአወናባጅነታቸው የሚታወቁት አባ መላኩ (አቡነ ፋኑኤል) ናቸው።

በአቡነ ማትያስ የሚመራው “ሲኖዶስ” ቢያንስ ሚስቱን በአቶ ታደሰ የተነጠቀውንና ልጆቹ ካለ እናት እንዲያድጉ የተፈረደባቸውን ልጆች የእምባ ድምጽ በመስማት ትክክለኛ ፍርድ መስጠት ሲገባው ቀድሞ በሌሎች ሶስት ካህናት በምዕመናን ፊት የተወሰነውን ውግዘት እንኳ ለማጽናት ወኔው ከከዳው ሁለት ዓመታት አለፉ። የአቡነ ማትያስ ሲኖዶስ በዚህም ምክንያት በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 20 ቁጥር 28-30 የተጻፈው እየመሰከረባቸው እንደሆነ ለመገንዘብ አያዳግትም። “……..በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና

123

አባ መላኩ (ፋኑኤል) እራሳቸው የማይገባቸውን የፓትርያርክ ልብሰ ተክህኖ አድርገው በመታየት እስከዛሬ ሲፈጽሙ የኖሩት ማወናበዳቸውን አሁንም ቀጥለውበታል። ታደሰ ሲሳይ ላይ የተላለፈበት ውግዘትና ስልጣን ክህነት መገፈፍ ታፍኖ  አንዲቀር  ለማድረግ ትልቁን ሚና የተጫወቱት አባ መላኩ ሲሆኑ ከፍተኛ ግምት ያለው ጉቦ ከታደሰ ሲሳይ መቀበላቸውንና የምንኩስና ማዕረግ በማስጠቱ ሂደት ላይ ገንዘቡን “ለስራ ማካሄጃ” እንደጠቀሙበት የሚናገሩ ጉዳዩን የሚከታታሉ ምዕመናን መኖራቸው ተገልጾልናል።

ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።…”

12345

ከታደሰ ሲሳይ ጋር በጥቅም የተሳሰረውና ቀኝ እጁ የሆነው አቶ አወቀ የተባለው ግለሰብ በቤተክርስቲያን ስም ምዕመናንን አብሮ በመዝረፍ ላይ ይገኛል። ከአንድ ዓመት ተኩል ገደማ በፊት አዛውንቱ አወቀ በቤተክርስቲያን ገንዘብ የይገባኛል ሽኩቻ ምክንያት መስፍን በዙ ከሚባለው የወያኔ ተስፈኛ ጋር ተጣልቶ ሽጉጥ እስከመማዘዝ የደረሰ መሆኑ ይታወቃል። ምንም እንኳ መስፍን በዙ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ ለታደሰ ሲሳይ የሰራለት ቢሆንም ከአወቀ ሊበልጥበት ስላልቻለ አስወግዶታል። መስፍንም በመባረሩ በቋጠረው ቂም ምክንያት ወደ ሙግት እንዲገባ መገደዱ ታውቋል።

የታደሰን ጉዳይ ጠንቅቃችሁ እያወቃችሁ አባ መላኩንና ወያኔን ላለማስቀየም ወይም ኢትዮጵያ ከመመላለስ ያግደናል ብላችሁ እውነተኛውን ነገር ከመመስከር የተለጎማችሁ ካህናት አሁንም አልመሸባችሁምና የውግዘትና የተቃውሞ ድምጻችሁን አሰሙ እየተባላችሁ ነው። ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን በሊቢያ በረሃ ስለ ክርስቶስ ፍቅር መራራውን የሞት ፅዋ በጸጋ ሰማዕት ሆነው ለመላው ዓለም ሲመሰክሩና የክርስትናን ሰንደቅ ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ እያያችሁ እናንተ ግን በጣም ትንሹን መስዋዕትነት እውነቱን መመስከር እንዳትችሉ የስጋችሁ ገመድ አስሯችሁ እስከ መቼ ነው የምትቀጥሉት??? ክርስትና የማይጨበጥና የማይዳሰስ ፅንሰ-ሀሳብ አይደለም። ክርስትና በሁሉም መንገድ የሚገለጽና ጽናትን የሚጠይቅ እንዲሁም መስዋዕትነትንና ተግባርን የሚጠይቅ ሐይማኖት ነው። ክርስትና እውነቱን ተናግሮ የመጣውን የሚቀበሉበት እንጅ ተመሳስሎና ተቀላቅሎ የሚኖሩበት ዓለማዊ ገበያ አይደለም። ስለሆነም ከሁለት ሽህ ዓመታት አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ታላቅ መስዋዕትነቶች እየተከፈሉባት ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ ቁርጠኛና ጠንካራ አባቶችን የምትፈልግበት ሰዓት አሁን ነው። ለቤተክርስቲያኒቷ መደረግ ያለባቸው አስተዋጽኦዎች ገቢራዊ መሆን የሚገባቸው አሁን እንጅ ይዋሉ፣ ይደሩ የሚባሉ አይደሉም። ከሁለት ዓምታት በፊት የታወጀውን ውግዘት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የቀድሞው ቀሲስ ታደሰ ሲሳይ ሥልጣነ ክህነታቸውን ተገፈፉ