የኦሕዴድ የብኣዴን አመራሮችና አባላት በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች መሪነት ግምገማ ተቀምጠው እየተናከሱ ይገኛሉ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የኦሕዴድ የብኣዴን አመራሮችና አባላት በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች መሪነት ግምገማ ተቀምጠው እየተናከሱ ይገኛሉ::
የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ ተከትሎ ኦነግ እና ለውጥ ፈላጊው ሃይል የኦሕዴድን መዋቅር ተጠቅሞ በኢሕኣዴግ ላይ ሕዝቡን አሳምጿል ድርጅታችንን ገበናውን አጋልጣችሁ ሰጣችኋል ወዘተ በሚሉ አጠቃላይ ወቅታዊ የኦሮሚያ ጉዳይ ዙሪያ የኦሕዴድ አመራሮችና አባላት(ካድሬዎች)በተለያዩ የስብሰባ ማእከላት በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች መሪነት ግምገማ ተቀምጠው እየተናከሱ ይገኛሉ::
ይህ ኢሕኣዴግ በሕወሓቶች ኦሕዴዶች ይገምገሙ ብሎ የሰጠው መመሪያ የኦሕዴድ አመራሮች በተለይ ራሳቸውን ለመከላከል አቅም ያጡበት እርስ በእርስ እየተኮራኮሙ የሕወሓት ገምጋሚዎች መሳቂያ መሳለቂያ የሆኑበት መሆኑ ታውቋል::በአዲስ አበባ የሚካሄደን የአመራሮች ግምገማ የሚመሩት የሕወሓት ከፍተና የፓርቲ ሹም በከፍተኛ የኦሕዴድ ባለስልጣናት እና በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሲሳለቁ ሲስቁ ተስተውሏል::በዝግ የሚካሄደውን ይህ የግምገማ መድረክ በርካታ አመራሮች ከቦታቸው እንደሚነሱ እና በሙስናም እንደሚከሰሱ ከወዲሁ እየተነገረ ይገኛል፡፡ባለፈው ሳምንት በሕወሓት ትእዛዝ ሁለት ከፍተኛ የኦሕዴድ ባለስልጣናት ከስልጣን መባረራቸው ይታወሳል::
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁ በሕወሓቶች እየተገመገመ ሲሆ የክልሉን ፕሬዚዳንት ጨምሮ ከፍተኛ የድርጅቱ ባለስልጣናት ይባረራሉ ይከሰሳሉ የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ ከቅማንት ማኅበረሰብ ማንነት ጋር በተያያዘ የተከሰተውን ችግርና የግጭት አፈታት ተግባራትን፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች በወልቃይት እና ጠገዴ ወረዳዎች የተከሰተውን ችግርና በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረው አለመግባባት በተመለከተ የብኣዴን አመራሮች እና አባላት ሚና እየተገመገመ ይገኛል::