አለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች ምነው ይህን ቱባ ዜና ዝም አሉ::ሕዝብ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተሰላችቷል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች ምነው ይህን ቱባ ዜና ዝም አሉ::ሕዝብ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተሰላችቷል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Eritrea‬ ‪#‎TPLFHoax‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Change‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ወያኔ የገባበትን አጣብቂኝ እና የሕዝብ ተቃውሞ መወጣት ሲያቅተው አቅጣጫ ማስቀየሪያ ዘገባ በፈጠራ ኤርትራን ደበደብኩ ሲል የለመደውን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መንዛት ጀምሯል::ከዚህ ቀደም የወርቅ ማእድን ማውጫውን ድባቅ መታሁ ሲል ተጋልጦ ሊያድበሰብስ ማለመቻሉ ምንተእፍረቱን ዝም አለ::ቀጣይነት ያላቸው ውሸቶች እና የሃሰት ፕሮፓጋንዳዎች ቢደሰኩር ሰሚ ባለማግኘቱ ሲያቅራራ እና ሲፎክር እዚህ ደርሷል::

Minilik Salsawi's photo.

በሰለጠነ ዘመን በቴክኖሎጂ የታገዙት አለም አቀፍ ታዋቂ የመገናኛ ብዙሃን እንዲህ አይነቱን ዘገባ ደበደበ የተባለው አየር ተመልሶ ሳያርፍ ነበር በሰበር ዜና የሚያራግቡት…ወያኔ ያላስተዋለው ነገር ቢኖር ሕዝብ ከአገዛዙ በላይ አገዛዙ ራሱን በባዶ እንደሚያንቆለጳጵስ በደንብ ጠንቅቆ ያውቃል::የኢትዮጵያን ሕዝብ ሳይሆን ራሳቸውን እየሸወዱ ነው::

ወያኔ ዛሬ ወፍ ዝር ባላለበት ኤርትራ ጀግናው አየር ኃይላችን ምፅዋ ሒርጊጎ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሻዕቢያ ወታደራዊ ቤዝ የግንቦት7 እና የደምሒት ማሰልጠኛ ማዕከል እና የኤርትራ ኤሌክትሪክ ግሪድ ማዕከል ላይ በወሰደው የአየር ድብደባ ጥቃት የሻዕቢያ የሸብር ማከፋፍያ ማዕከሎችን አወደመ ::ሲል የለመደውን ቅጥፈት ደስኩሯል::ይህን የመሰለ ቱባ ዜና እንደ ቢቢሲ እና ሲኤንኤን የመሳሰሉ የዜና አውታሮች እንዴት በቸልታ አለፉት::ያልሆነ ያልተከሰተ ጉዳይ ስለሆነ ወፍ ዝር ባላለበት ሚጎቼ አወደሙ ቢል የሚሰማው የለም::ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ማለት ይህ ነው::ባልተደረገ ተግባር ላይ ማቅራራት ወያኔ ምን ያህል ባዶ እንደሆነ ያመለክታል::ኧረ እየተስተዋለ ውሸትም እኮ አይነት አለው::ወያኔ ራሱን እንዴት እንደሚገምት አላውቅም::ሕዝቡ ከወያኔ የሃሰት ፕሮፓጋንድ ቀድሞ እንደሄደ አያውቁም :: ኧረ እየተስተዋለ !!!