በዛሬው እለት በበኒ መስጅድ ከፍተኛ ፍተሻና ወከባ መደረጉ ታወቀ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
BBN መረጃ
የካቲት 25/2008 ጁሙዓ
√=በዛሬው እለት በበኒ መስጅድ ከፍተኛ ፍተሻና ወከባ መደረጉ ታወቀ
√= የአንዋር መስጅዱ ኢማም ኮማንደር ጡሃ ዛሬ በአንዋር አስገራሚ ንግግር አደረገ
የሙስሊሞችን የእምነት ነፃነት መብት በሃይል እና በአፈ ሙዝ ረግጦ እየቀማ ያለው ኢሓዴግ መራሹ መንግስት በዛሬው እለት በአዲስ አበባው በኒ መስጅድ ተቃውሞ ሊደረግ ይችላል በሚል ስጋት እና ጥርጣሬ በመስጅዱ መግቢያና አካባቢ በርካታ ፓሊሶች እና ደህንነቶችን አሰማርቶ ሙስሊሞችን በፍተሻ እያዋከበ እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል ።
እንደምንጮቻችን ተጨማሪ ገለፃ መሰረትም ባለፉት ግዜያት በአንዋር እና ፍልውሃ መስጅዶች በተደረገው ከፍተኛ ተቃውሞ ድንጋጤ ያደረበት መንግስት ይሄው ተቃውሞ ዛሬ በበኒ መስጅድ ሊደገም ይችላል በማለት እና በመስጋት ፓሊሶች እና ደህንነቶችን አሰማርቶ በሙስሊሙ ላይ ለየት ያለ ፍተሻና ወከባ መፈፀሙ ታውቆ በተለይም መስጅዱ ሞልቶባቸው ውጭ ላይ መስገጃ አንጥፈው ለመስገድ የሞከሩ ሙስሊሞችን ውጭ ላይ አንጥፋችሁ መስገድ አይችሉም በማለት ፓሊሶችና ካድሬዎች ወከባ ሲፈፅሙ እንደነበር ተዘግቧል
ይህ በእንዲህ እንዳለም በዛሬው ጅሙዓ የአንዋር መስጅዱ ኢማም ኮማንደር ጡሃ ሃገራችን ሰላም ናት መንግሥታችንም ጥሩ ነው በአራቱም አቅጣጫ ምንም ችግር የለም ፣ ሀገራችን በኢኮኖሚውም አድጋለች የህዝቦች መብት ተከብሯል በማለት በግልፅ የፓለቲካ ቅስቀሳ ተልዕኮውን መፈፀሙ የታወቀ ሲሆን በተለይም የመብት ጠያቂዎችን ” ነውጠኞች ” እና “የሃገር ሰላም የማይፈልጉ “በማለት እና በመፈረጅ መናገሩን ምንጮች ለቢቢኤን ገልፀዋል
ከዚህም በተጨማሪ ኮማንደር ጡሃ በዛሬው ንግግሩ የመጅሊስ አካላት በከፍተኛ የሙስና ተግባር ውስጥ ተዘፍቀዋል የህዝቡን ገንዘብ እየዘረፉት ነው በማለት የተናገረ ሲሆን በተመሳሳይም የአንዋር መስጅድ አስተዳደር የሆነው አቶ ሸምሱ የመስጅዱን ገንዘብ ዘርፎ እየጨረሰው መሆኑን በይፋ አጋልጧል ።
ኢንሻ አላህ ዝርዝር መረጃዎችን በምሽት ፕሮግራማችን ይዘን እንቀርባለን
