የኦሮሚያ ክልል ጭር ብላለች::መንገዶች እና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ተዘግተዋል::ተቃውሞው ቀጥሏል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ራሱ በሰራው ወንጀል ሕወሓት ሕዝብ አይነካ ብለዋል የተባሉትን የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ካባረረ በኋላም የሕዝብ ተቃውሞ መብረድ አልቻለም::በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል የተሰበሰበው ሪፖርታዥ እንደሚያመለክተው በከፍተኛ ደረጃ ቆራጥ የኦሮሞ ልጆች ለመብታቸውና ለነጻነታቸው ያላቸው የለውጥ ተስፋ በትግላቸው ሕያው ለማድረግ ተቃውሞውን ቀጥለው የዋሉ ሲሆን የዛሬ በኢትዮጵያ የተከሰቱት ተቃውሞዎች ለያት የሚያደርጋቸው የወሎ ክፍለ ሃገር የአሽከርካሪዎች አድማ እና የጎንደር የወልቃይቶች አንድነት ለመጪው የለውጥ ተስፋ ብርሃናቸውን ሲያበሩ ውለዋል::የወያኔው አገዛዝ ከመደናገጡም በላይ እንደለመደው ሲያስር ሲገድል እና ሲደበድብ ብሎም ደህንነቶቹን አሰማርቶ መረጃ ሲሰበስብ ውሏል::
ባለፈው ሁለት ቀን የትራንስፖርት እና የመንገድ መዝጋቱ በተጀመረባቸው አከባቢዎች የቀጠሉ ሲሆን ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ከአሰላ ወደ አዳማ ናዝሬት የሚያስገባው መንገት በትልልቅ የድንጋይ አለቶች የተዘጋ ሲሆን የአግኣዚ ጦር የአከባቢው ሚሊሻዎች ድንጋዮቹን አንስተው መንገዱን እዲከፍቱ ሲያስገድዱ ውለዋል::በምእራብ ሸዋ ዱግዳ ወረዳ መቂ አከባቢ ከኦሮሞ ገበሬዎች ተነጥቆ በሕወሓት ሰዎች የሚተዳደሩ እርሻዎች በሕዝቡ ተቃውሞ ለሊቱን ተደምሥእው አድረዋል::በቦረና ድቡሉቅ ከተማ ሕዝቡ ተቃውሞ ሲያሰማ የዋለ ሲሆን በአዲስ አበባ ሰበታ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁ ተቃውሞ አሰምተዋል::በወለጋ ዩንቨርስቲ ለሁለተኛ ቀን ለሊቱን የጀመረው የተቃውሞ ድምጽ እስከጠዋት ቀጥሎ እንደነበር ሲታወቅ የአጋዚ ወታደሮች ተማሪዎችን ሲደበድቡ እና ሲያንገላቱ እንደነበር ተጠቁሟል::
በኢሉባቦር በመቱ ከተማ ሁለተኛ ደረጃና የቴክኒክ ሙያ ተማሪዎች በዛሬው እለት ከፍተኛ ተቃውሞ ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን : የመንግሰት ሃይሎች በወሰዱት እርምጃም ብዛት ያላቸው ሰዎች መጎዳታቸው አንድ የከተማው ነዋሪም በጥይት ተመቶ ህይወቱ ማለፋ ታውቋል ።በተመሳሳይ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከትናንት ወዲያ ጀምሮ ማታ ላይ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።በወያኔ አጋዚ ወታደሮች በተወሰደ እርምጃ የተጎዱና የታሰሩ መኖራቸው የታወቀ ሲሆን በዛሬው እለትም የታሰሩ ተማሪዎች መኖራቸው ታውቋል ።በተየያዘ ዜናም በጅማ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ሰአት ተቃውሞ ተነስቶ ረብሻ መፈጠሩ ታውቋል።ለአራት ወር ያክል በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው የአጋዚ ጦርም በተማሪዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል። #ምንሊክሳልሳዊ