የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች በጎንደር ስብሰባ ተቀመጡ::የሕወሓት የ30 አመት ወንጀሎች ተተንትነዋል:: Minilik Salsawi


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች በጎንደር ስብሰባ ተቀመጡ:: የሕወሓት የ30 አመት ወንጀሎች ተተንትነዋል:: Minilik Salsawi

በሕወሓት የተዘረፈባቸውን ማንነት እና መሬት ለማስመለስ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች በጎንደር ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል::
በጎንደር ከተማ ላንድ ማርክ ሆቴል ዛሬ የተካህደው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች ስብሰባ ቁጭት እና እልሕ የተሞላበት ነበር::ይህ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ አድርጎ ያሳየ በሳል እና ታሪክ ውቃኢ የወልቃይት የሃገር ሽማግሌዎች የመሩት ስብሰባ ሕወሓት በሕዝቡ ላይ የሚፈጽመው ወንጀል በዝርዝር ተደምጧል::

በስብሰባው የተካፈሉ ወገኖች እንዳሉት አማራ ትግሰተኛ እንጅ ፈሪ አደለም::አማራ ዝምታው ኢትዮጵያዊነት ይበልጣል ብሎ እንጅ ያውቅበታል፡ጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ድርድር ውሰጥ የሚቀርብ ጉዳይ አደለም የበጌምድር ጎንደር አማራ መሪት ነው ።ዛሪ ከተካሄዱት ቁጭት እልህ የተሞላበት ስብሰባ ኢትዮጵያውነትን ዛሪም እንደትላንቱ ያሰቀደመ በሳል አባቶች ያካሄዱት ሰብሰባ።በወልቃይት ህዝብ ያደረገው ዘርማጥፋት አየተነገረ ነው። ናዚ ትግሬ ወያኔ በአለም ታይቶ በማይታውቅ ሁኔታ በወልቃይት ህዝብ ላይ ላለፉት 30 አመታት አጅግ ዘግናኝ ግፍ ሰርቶል። ይሄን ያደረገውም የጎንደርን ለም መሬት ለመውሰድ ነው። ወገን ከዚህ በላይ ምን አስኪሆን ነው የምንጠብቀው።የሚሉ ድምጾች ይተደመጡ ሲሆን በስብሰባው ላይ የተካፈሉ የብኣዴን ካድሬዎች ቁጭት እና ብስጭት ይነበብባቸው ነው:: #MinilikSalsawi