በደሴ እና በአቅራቢያ ከተሞች የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በደሴ እና በአቅራቢያ ከተሞች የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል::
#Ethiopia #Dessie #TaxiDriversStrike #MinilikSalsawi #Freedom #Change

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከወሎ ክፍለሃገር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በደሴ እና አከባቢው ከተሞች የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል::የወያኔ ፖሊሶች እና ካድሬዎች ታርጋ እየፈቱ ቢገኙም ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው::በዚህም መሰረት ደሴ ከ4 መቶ የማያንሱ ታክሲ እና ከ 3 መቶ በላይ ባጃጆች አሏት ዛሬ ጥቂቶች ናቸው የሰሩት አድማው ከሰአት ቡሀላ ተተናክሮ ይቀጥላል ተብሏል በሚሰሩ መኪኖች ላይ እርምጃም እንወስዳለን ብሏል ህዝቡ::
ከአሽከርካሪዎች ጋር በመተባባር እርምጃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ነጻነት የናፈቀው የደሴ የወልዲያ እና የአከባቢው ከተሞች ሕዝብ ከአሽከርካሪዎች ጎን መቆሙን በተግባር አሳይቷል::በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ከአሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘ የወያኔ አገዛዝ ከፍተኛ የሆነ የመብት ገፈፋ እንደሚያካሂድ የታወቀ ሲሆን የትራፊክ ፖሊሶች በዘረፋ ላይ መሰማራታቸው በተደጋጋሚ እየተነገረ ይገኛል:: የአዲስ አበባ የታክሲዎችን አድማ ተከትሎ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ከፍተኛ የሆነ መተባበሮች እና አድማዎች ቀጥለዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ


