በወልቃይት ጠገዴ ውጥረቱ የተባባሰ ሲሆን ሕወሓት 70ሺህ የትግራይ አባወራዎች ሰፈራ ሊተገብር ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በወልቃይት ጠገዴ ውጥረቱ የተባባሰ ሲሆን ሕወሓት 70ሺህ የትግራይ አባወራዎች ሰፈራ ሊተገብር ነው::
#Ethiopia #TPLF #Welkaite #Tigray #Amhara #Freedom #Miniliksalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ቀብር/ለቅሶ እንሂድ ሲሉት ሰው ነው ትግሬ የሞተው የሚለው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የማልፈልገው እና ያልሆንኩት የትግራይ ማንነት በግዴታ ተጭኖብኛል በሚል የጀመረው ትግል ተጠናክሮ መሄዱ የአከባቢውን ውጥረት እንዲባባስ ማድረጉን እና መፍትሄ ካልተገኘለት በሕወሓት ላይ ከባድ አደጋ እና ኪሳራ እንደሚሆን በአከባቢው የሚኖሩ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች በመናገር ላይ ይገኛል::ከቦታው ምንሊክ ሳልሳዊ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እና ለስራ በአከባቢው የሚገኙ እንደሚጠቁሙት የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ትግል የሰለጠነ ነው እደነሱ በጉልበት እና በሃይል መግፋት ላይ ያተኮረ አይደለም ባለንበትም ስፍራ ይሁን በአለማቀፍ የዲፕሎማሲ መንገድ አሸናፊነታችንን በተግባር አረጋግጠናል ከተከዜ ምላሽ ማናውም የትግራይ አስተዳደር ማለፍ የለበትም ተሰብስበው ይቀመጡ በማለት ወጣቶች እና የሃገሩ ሽማግሌዎች አሁንም ለሕወሓት ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ይገኛል::በሕዝብ ላይ በደል እና ግፉን ማድረግ የቀጠለው የሕወሓት አገዛዝ የሕዝቡን ሃሳብ በፍጹም ሊቀይረው አልቻለም::
የትግራይ ተወላጆች ወልቃይትን ለቀው እየወጡ ነው ሊወጡ ነው የሚል ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ በተዘዋዋሪ ባልበሰሉ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ዘንድ የሚያስነዛው ሕወሓት በተለያዩ የወልቃይ ጠገዴ ጋምቤላ ቤንሻንጉል ጉምዝ አከባቢዎች 70ሺህ የትግራይ አባወራዎችን ሰፈራ በተግባር ሊሰራ ሲሆን በድርቅ እና በድህነት ከተጎዱ የትግራይ አከባቢዎች ተነስተው የሚሰፍሩት የትግራይ ተወላጆች በሕወሓት በሚሰጣቸው መሳሪያ ራሳቸውን እንዲከላከሉ እና ንብረታቸውን እንዲጠብቁ እንደሚደረግ ተሰምቷል::የተለያዩ የኢትዮጥያ ለም አከባቢዎች የትግራይ ተወላጆች ሰፈር በስፋት እንደሚደረግ የታወቀ ሲሆን በኦሮሚያ እና በደቡብ ኢትዮጵያም ይህንኑ ሰፈራ ለመተግበር የሚደረጉ የመስክ ጥናቶች መጀመራቸው ታውቋል::
የወልቃት ሕዝብ እስሩን በደሉን እና ጭቆናውን ችሎ የሕወሓትን አገዛዝ እየተፋለመ የሚገኝ ሕዝብ ሲሆን በተለያኡ የሃገር ውስጥ እና የአለም አቀፍ መድረኮች በድል እየተራመደ የሚገኝ ሕዝብ ነው:: የወልቃይት ሕዝብ ራሱ የሚያደርገውን ትግል ራሱ እያሸነፈ በድል የሚወጣበትን ትግል የራሳቸው አድርገው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚውተረተሩ በባዶ ፕሮፓጋንዳ የሚናውዙ ፖለቲከኞች እና ድርጅቶች ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው ሲሉ ምንጮቹ የተናገሩ ሲሆን የሕወሓት አገዛዝ በሕዝብ ትግል ከአከባቢው እንደሚነቀል ተናግረው አብረውን የኖሩ የትግራይ ተወላጆችን ግን ይህ ጉዳይ አይመለከትም እውነቱን ስለሚያውቁት ከጎናችን የቆሙ ነዋሪዎች አሉ ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ