ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና እየተስፋፋ የመጣውን ‪#‎OromoProtest‬ በማስመልከት የኣውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፕሬዚዳንት በቀጥታ የሰጡት መልስ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና እየተስፋፋ የመጣውን ‪#‎OromoProtest‬ በማስመልከት የኣውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፕሬዚዳንት በቀጥታ የሰጡት መልስ

የተከበሩ ኣቶ Decke,
በኢትዮጵያ የኦሮሞን ማህበረሰብ ወቅታዊ ሁኔታ ኣሳሳቢነት በመግለፅ ጥር 14, 2016 የላኩልኝን ደብዳቤ እንዳገኘሁት ላረጋግጥሎት እወዳለሁ። የኣውሮፓ ፓርላማ ይህ ኣሳሳቢ ሁኔታና በኢትዮጵያ ያለው የሰብኣዊ መብት ረገጣ እንዲሻሻል ማንኛውም ነገር መደረግ እንዳለበት በጥብቅ ያምናል።

Hamza Borana's photo.

የኣውሮፓ የውጭ ጉዳይ ፖለቲካ ከመሰረታዊ ሃሳቦቹ ኣንዱ የሰብኣዊ መብቶች በ3ኛ ሀገሮች መከበር ላይ የተገነባ ነው።

እንደሚታወቀው የኣውሮፓ ፓርላማ በጥር 21, 2016 ባስተላለፈው ውሳኔ እንደሚከተለው ይላል:
[የኣውሮፓ ፓርላማ] ,, በቅርቡ በኦሮሚያና በሌሎች የኢትዮጵያ ኣካባቢዎች ባለው ሁኔታ የደህንነት ጠባቂዎች የሚያሳዩትን ጭካኔያዊ ኣካሄዶችና የሰብኣዊ መብት ረገጣዎች በጥብቅ እናወግዛለን: ለተጎዱትም ሃዘናችንን እየገለፅን መንግስት የሁሉንም የመሰባሰብና የነፃ ሃሳቦችን የማንሸራሸር መብት እንዲያከብር እንዲሁም የታሰሩት በቶሎ እንዲፈቱ እንጠይቃለን,, በተጨማሪም የኣውሮፓ ፓርላማ የኢትዮጵያን መንግስት የኣፍሪካን ቻርተርና ሌሎች ኣለም-ኣቀፋዊ የሰብኣዊ መብት ስምምነቶችን እንዲሁም የCantonou ውል በተለይ በኣንቀፅ 8 እና 96 መከበር ያለባቸውን መብቶች ፍትህ የማግኘትና የፍትህ ሂደቶችን ሙሉ መብት ማክበር እንዳለበት ልናሳስብ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ መንግስት ማንኛውንም የሰብኣዊ መብት ስምምነቶች እንዲሁም የኦሮሞን ህዝብ መብቶች እንዲያከብር ለማስገደድ የኣውሮፓ ፓርላማ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን።
ከክብር ሰላምታ ጋር
ፊርማ
ማርቲን ሹልዝ