አዲስ አበባ የሥራ ማቆም አድማ ተደረገ ፤ ከዚህ በኋላ ? ግርማ ካሳ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አዲስ አበባ የሥራ ማቆም አድማ ተደረገ ፤ ከዚህ በኋላ ? ግርማ ካሳ
ገዢዎች በሃረርጌ፣ በወለጋ፣ ጉጂ፣ ቦረና፣ በምእራብ ሽዋና ምእራብ አርሲ የተነሳዉን ተቃዉሞ ከፍተኛ ቁጠር ያለው የወታደር ኃይል በማሰማራት በመቶዎች የሚቆጠሩትን በመግደልና በሺሆች የሚቆጠሩትን በማሰር ተቃዉሞዉን በኃይል ለማፈን እየሞከሩ ነው። በአንዳንድ ሜዲያዎች እንደተዘገበው፣ የኦሮሚያ ክልል በስምንት ቀጣናዎች ተክፍላ በወታደራዊ እዝ ሥር ሆናለች። ከዚህም የተነሳ በኦሮሚያ ተቃዉሞው በአንዳንድ ቦታዎች ቢታይም በአንጻራዊነት ለጊዜዉም ቢሆን በብዙ ቦታዎች ጋብ ያለ ይመስላል።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ተቃዉሞዎን ተቆጣጥጥረነዋል ሲሉ ነበር ፣ ተቃዉሞው ግን እንደገና አገረሸ፡፡ በመሆኑም የሕዝብ መሰረታዊ የመብት ጥያቄ እስካልተነሳ ድረስ ፣ ወደፊትም ተቃዉሞ ተመልሶ የማይመጣባት ምንም ምክንያት አይኖርም።
በኦሮሚያ ያለው ሁኔታ ይህን ሲመስል ዛሬ ደግም በአዲስ አበባ የታክሲዎች የሥራ ማቆም አድማ ተጀምሯል። አድማው በጣም የተሳካ እንደነበረ ነው የሚደርሰን መረጃ የሚገልጸው። አሁንም ገዢዎች የኃይልና የጡንቻ እርምጃ እየወሰዱ ነው። የቆሙ ታክሲ ነጂዎችን ታርጋ በኃይል በመንቀል ለማስፈራራት እየሞከሩ ነው። ከጥቂት ሰዓትታ በኋላ በሚቆጣጠሩት ኢቢሲ/ኢቲቪ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን የሚል የማስፈራራት መግለጫዎችን ሊያሰሙ ይችላሉ።
መረጃዎች እንደሚጠቁሙትም የታክሲ ነጂዎች የሥር አማቆም አድሞ ነጋዴዎችና ተማሪዎችም ሊቀላቀሉት ይችላሉ። ትራንስፖርት የለም፣ ንግድ የለም፣ ትምህርት የለም በሚል ዘመቻ።
በነገራችን ላይ ታክሲዎች ያደረጉት የሥራ ማቆም አድማ ሕገ ወጥ አይደለም። በሕገ መንግስቱ የተደነገገ፣ በሰለጠኑ አገሮች የተለመደ ዴሞክራሲያዊ መብት ነው። በመሆኑም ይሄንን እንቅስቃሴ ወያኔዎች ከግንቦት ሰባት፣ ሻእቢያ፣ የጥፋት ኃይሎች ከሚሏቸው ጋር በማገናኘትት በሌላው መሳቂያ ባይሆኑ ይሻላቸዋል። ይህ እንቅስቃሴ ፍጹም ሰላማዊ የሆነ እንቅስቃሴ ነው። ሰላማዊ ትግል አይሰራም የሚሉ ወገኖችን በድጋሚ ኖት ቢወስዱ ጥሩ ነው።
ይሄን ብዬ ለወያኔዎች ትንሽ መልእክት ላስተላልፍ። መቼም ሰዎቹ ድንጋይ ራስ ስለሆኑ አይሰሙም እንጂ። ፡)፡) “ ከሕዝብ ጋር መጋፈጥ አይበጃችሁም። በተለያዩ ሰበቦች የሚነሱት ተቃዉሞዎች ሥር መሰረታቸው የናንተ ግፋዊ አገዛዝ መሆኑን ተረድታችሁ በወሬ ሳይሆን በተግባር ለዉጥ ማምጣት አለባቸው። ለብሄራው እርቅ መዘጋጀት አለባቸው። የዘር ፖለቲካዉን የዘር አወቃቀሩን ቀይሩ፣ ከዚህ በኋላ ዜጎች በዘር ሳይሆን በስብእናቸዉና በሥራቸው ነው መመዘን ያለባቸው። አገር ቤት ካሉ ሰላማዊና ሕጋዊ ተቃዋምሚዎች ጋር ሆናችሁ የአንድነት ወይንም የሽግግር መንግስት መስርቱ። የታሰሩትን ሁሉ ፍቱ“ እላቸዋለሁ።
ወያኔዎች፣ ምናልባት ታክሲ ነጅዎች ሶስት፣ አራት ቀናት ከቆዩ በኋላ የሚበሉት ሲያጡ ስራቸውን ይጀምራሉ የሚል አስተሳሰብ ሊኖራቸው ይችላል። መብራት እያጠፉ በጨለማ የሚያስቀመጡት የአዲስ አበባ ነዋሪ ትራንስፖርት አገኘ አላገኘ ለነርሱ ብዙም ላያሳስባቸው ይችላል። እንዳሰቡት ሊሆን እና በቀላሉ ተቃዉምሞዉን ሊቆጣጠሩት ይችልሉ። ግን ደግሞ የታክሲዎች አድማ እንደተባለው ወደ ተማሪዎችና ወደ ንግዱ ማህበረሰብ ከተሸጋገረ፣ በሁሉም ወረዳዎች ቁጣ መቀስቀሱና ህዝቡ የአራት ኪሎን ቤተ መንግስት አጥር ገንድሶ መግባቱ አይቀሬ ነው። በቻዉቼስኮ ላይ እንደሆነው። ልቦና ይኑራቸው እላለሁ።