በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ተቃውሞ በታክሲ ሹፌሮች አድማ ታጅቦ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል:: በወሊሶ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ እየጋየ ነው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ተቃውሞ በታክሲ ሹፌሮች አድማ ታጅቦ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል::
#Ethiopia #Oromoprotests #AddisAbaba #TaxiDriversStrike #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) እምቢ ለመብቴ ግፍ ይብቃ የሚለው ሕዝብ እየበረከተ ተቃውሞው እያሰማ መሆኑን እና መቀጠሉን ከኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክል የሚወጡ መረጃዎች የጠቆሙ ሲሆን ተማሪዎች ገበሬዎች እንዲሁም የከተማ ነዋሪእዎች የወያኔ አገዛዝ ላንዴና ልመጨረሻ ጊዜ እንዲወገድ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን አገዛዙ በጭቆና ቀንበር ስር አድርጎ መብት እና ነጻነትን እየገፈፈ መሆኑን አበክረው እየገለጹ ይገኛሉ::
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተካሄደው የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ በሸዋ ሰላሌ እና በአርሲ በቆጂም እንዲሁም በሆለታ የባጃጆች የስራ ማቆም አድማ የተደረገ ሲሆን በቀጣይነት በተለያዩ ከተሞች ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል::በምእራብ ወለጋ በሆሮ ጉዱሩ በአምሩ ከተማ ተማሪዎች ተቃውሞ ያደረጉ ሲሆን በቦረና ዞን ሜጋ ከተማ በአርሲ ዝዋይ ዱግዳ ወረዳ ጠንካራ ተቃውሞ ተደርጎ ውሏል::በተለያዩ የሃርረጌ አከባቢዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአግኣዚ ወራሪ ጦር እንዲሰፍር የተደረገ መሆኑ ታውቋል::የአዲስ አበባን ታክሲዎች አድማ በመተባበር በተፍኪ መንገድ የተዘጋ ሲሆን በወሊሶ እና ፍቼ መናሃሪያ የገባም የወጣም አውቶብስ አለመኖሩ ተረጋግጧል:: የወያኔው ወራሪ ጦር በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ግፍ መፈጸሙን ቀጥሏል::
ኢትዮጵያ አብዮት አብዮት ትሸታለች።ነጋዴዎችና ተማሪዎች አድማውን ሊቀላቀሉ ነው ::በአዲስ አበባ የተጀመረው የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ፣ ነጋዴዎች እና ተማሪዎች በነገው እለት ሊቀላቀሉ ነው፨ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት አድማውን ሳይቀላቀሉ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታክሲዎች አድማውን የተቀላቀሉ ሲሆን፤የተቀሩት ደግሞ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መስታወታችው እየተሰበረ እንደሆነ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በወሊሶ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ዙሪያ እየጋየ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። እስከአሁን የካምፓሱ አስተዳደር እና የተማሪዎች መኝታ ቤቶች ጋር አልደረሰም። እሳቱን ለማጥፋት ተማሪዎችንና የዓካባቢው ነዋሪዎች ርብርብ እያደረጉ ነው።