ታላቋ ምሁር ዶክተር ማይገነት ሽፈራሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


http://www.ethiopianreview.com/index/wp-content/uploads/Dr-Maigenet-Shiferraw.jpg

 

በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በዶክተር ማይገነት ሽፈራሁ ሞት ምክንያት ከባድ ሐዘን ላይ ናቸው። ዶክተር ማይገነት ሽፈራሁ የዶክተር ጌታቸው መታፈሪያ ባለቤትና የትዕግስት፣የህሊናና የካሌብ እናት ነበሩ። ዶክተር ማይገነት ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብኣዊ መብቶች እንዲሰፍኑና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ያላሰሰ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የሚታወቅ ነው። ኢትዮጵያን ሪቪው በዶክተር ማይገነት ሞት ምክንያት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለመላው የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ኢትዮጵያዊያን እየገለጸ አግዚያብሔር ነፍሳቸውን በጻድቃንና በሰማዕታት አጠገብ ያሳርፍልን በማለት የሐዘን መልዕክቱን ያስተላልፋል።

የፍትሐት ጸሎት በቅዱስ ገብርኤል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ ሰኞ ፌብርዋሪ 29, 2016 ከጠዋቱ 10 AM እስከ 1 PM ድረስ ይካሄዳል።
የቤተክርስቲያኑ አድራሻ 2601 Evarts St. NE
Washington DC 20018
የቀብር ስነ ሥርዓት 2 PM George Washington Cemetery
9500 Riggs Road
Adelphi, MD 20783