የሕዝባዊ እምቢተኝነት ንቅናቄ በኦሮሚያ ሲቀጥል በኦሕዴድ ላይ የተደረገው መፈንቅለ መንግስት አባላቱን አስደንግጧል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የሕዝባዊ እምቢተኝነት ንቅናቄ በኦሮሚያ ሲቀጥል በኦሕዴድ ላይ የተደረገው መፈንቅለ መንግስት አባላቱን አስደንግጧል:: #Ethiopia #Oromoprotests #OPDO #TPLFArmy #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – UPDATE – ኦሮሚያ ክልል የጦር ቀጠና መሆኗ ታውቋል::የኦሕዴድ አባላት ማጉረምረም የጀመሩ ሲሆን ድርጅታቸውን እየጣሉ ከሕዝቡ ጎን መቆም መቀጠላቸው ሲሰማ ይበልጥ የልማት ሰራተኞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የወያኔ ጦር መመሪያ እንደተላለፈለትም አብሮ የተሰሙ መረጃዎች የጠቆሙ ሲሆን በዛሬው እለት በቦረና ዞን ሂዲ ሎላ ቴሶ ቀበሌ በሚገኝ የሁለተኛ ደረጃ ትምርት ቤት ተማሪዎች ተቃዉሞ አደረጉ።በሂዲ ሎላ የገበያ ቀን በመሆኑ የኦሮሚያ ፖሊስ በቦታው ያልነበሩ ሲሆን ነገር ግን ከቴሶ ቀበሌ ወደ ገበያ የሚመጠትን ተማሪዎች እየመረጡ ሲደበድቡ ነበር ።ዛሬ በተደረገው ቴሶ ቀበሌ ላይ ከ50 በላይ ሰዎች የተደበደቡ እና ዲባ ጌታ ዋቆ የተባለን የልማት ሰራተኛ (DA)አንተ ነህ ሰልፉን ያቀናጀሀው በማለት ክፉኛ ደብደበው ይዘውት ሄደዋል።
በሰላሌ ገብረጉራቻ ያለው የመለስ ዜናዊ እና የአለማየሁ አቶምሳ ፓርክ ወደ መጸዳጃነት መለወጡን እና ሕዝቡ ሽንቱን መሽናት ሲፈልግ ወደ ፓርኩ በመሄድ እንደሚሸና ነዋሪዎች ተናግረዋል::በኦሕዴዽ ላይ የተደረገው መፈንቅለ መንግስት (ዝርዝሩ:- http://www.mereja.com/amharic/485544 ) አባላቱን ማስደንገጡን ታውቋል::ሲቭል መስተዳደሩ ለስምንተኛ የምድር ጦር ዲቭዥን ስልጣኑን ማስረከቡን ተከትሎ አባላቱ ማጉረምረም ጀምረዋል::
