የውብሸት ወርቃለማሁ እና የብርሀነ ንጉሴ ጭምብል – የበርካታ እንስቶች ህልምን አጨልመዋል:: #(ኤርሚያስ ቶኩማ‬)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የውብሸት ወርቃለማሁ እና የብርሀነ ንጉሴ ጭምብል #‎ኤርሚያስ_ቶኩማ‬
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ በጭምብል የሚንቀሳቀስ ሰው መብዛቱ በተለይም እነዚህ ሁለት ግለሰቦች በየሚዲያው እየቀረቡ ሲያወሩ ለሚሰማቸው እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ፍፁም ቅንና መልካም ሰዎች መስለው ይታያሉ ውብሸት ወርቃለማሁ የሚፈራቸው ጋሽ ውብሸት ይላቸዋል እውነታው ግን ውብሸት ወርቃለማሁን አንቱ ማለት ኢትዮጵያን የደህና ሽማግሌዎች መሀን አድርጎ እንደመቁጠር ነው። ውብሸት ወርቃለማሁ ስለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ማውራት የሌለበት ነውረኛ ግለሰብ ነው የዚህ ነውሩ ተባባሪ ከሆኑት መካከል አንዱ ደግሞ ኢትዮፒካሊንክ የተባለ የሬድዮ ዝግጅት አዘጋጅ የሆነው ብርሀነ ንጉሴ ይገኝበታል።
ውብሸት ወርቃለማሁ የበርካታ ኢትዮጵያዊያን ወጣት እንስት ሴቶችን ህልም ያጨናገፈ እጅግ ለሌሎች ተምሳሌት መሆን የሌለበት ተራ ግለሰብ ነው ይህ ግለሰብ ሐገሪቱ ውስጥ ትክክለኛ የፍትህ ስርአት ቢኖር ለፍርድ መቅረብ የነበረበት አሳፋሪ ግለሰብ ነው።
የኢትዮፒካሊንኩ ብርሃነ ንጉሴና ውብሸት ወርቃለማሁ በጋራ በመሆን የበርካታ እንስቶች ህልምን አጨልመዋል ብርሃነ ንጉሴ በኢትዮፒካሊንክ ስም የቁንጅና ውድድር እያዘጋጀ በርካታ እህቶቻችንን ለውብሸት ወርቃለማሁ እና ለራሱ ገፀ በረከት ያደርጋቸው ነበር። በአንድ ወቅት ሀገር ቤት በሚታተመው ቃልኪዳን በተሰኘ መጽሔት ላይ ይሰራ የነበረ የቅርብ ጓደኛዬ በርካታ እንስቶች የመጽሔቱ የዝግጅት ክፍል ድረስ እየመጡ የደረሰባቸውን በደል ህዝብ እንዲያውቀው ለመጽሔቱ አዘጋጆች ቢያቀርቡም በውብሸት ወርቃለማሁ እና በብርሀነ ንጉሴ ጡጫ ነገሩ ችላ መባሉን በወቅቱ አጫውቶኝ ነበረ ይህ ሁሉ እያለ ሁለቱ ግለሰቦች በተለያዩ ሚዲያዎች እየቀረቡ እንደሀገር ወዳድ ስለአድዋ ድል ሲናገሩ ብሰማ አዘንኩኝ እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ስለኢትዮጵያ ሊያወሩ የማይገባቸው አሳፋሪ ዜጎች ናቸው። የአድዋ በአል በእነዚህ ተኩሎች ስም ሲጠራ የጀግኖች አባቶቻችን መልካም ስራ የቆሸሸ ያህል ይሰማኛል። አልፎ ተርፎም ያለማፈር እንደመልካም ግለሰብ የኢትዮጵያ የልኡክ ቡድን በመሆን ግብፅ ድረስ በመሄድ ስለአባይ ግድብ ጉዳይ የግብፅ የባለሥልጣናት ቡድንን አናግረዋል።
ለማንኛውም ለሁሉም ጊዜ አለው ሁሉም የዘራውን ያጭዳል ያ ቀን ደግሞ ቅርብ ነው ለሐገር ነው የቆምነው የሚሉ ሚዲያዎቻችንም የእነዚህን ነውረኞች ምግባር አደባባይ በማውጣት ነውራቸውን ህዝብ ሊያውቀው ይገባል።

Ermias Tokuma's photo.

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የነገሰም ይወርድና
ያጣም ያገኝና
ያስተዛዝበናል ይቺ ቀን ታልፍና።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አበቃሁ
‪#‎ኤርሚያስ_ቶኩማ‬