አስደሳች ዜና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከወህኒ ቤት ሶስተኛ መፀሃፉን ለኢትዮጵያን ሙስሊም አበረከተ!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አስደሳች ዜና #MinilikSalsawi

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከወህኒ ቤት ሶስተኛ መፀሃፉን ለኢትዮጵያን ሙስሊም አበረከተ!

የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆነው ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከወህኒ ቤት ሶስተኛ መፀሀፉ የሆነውን 3ቱ አፄዎች እና ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች(ትግል እና መስ ዕትነት) በሚል ያዘጋጀውን ታሪካዊ መፀሀፍ ለህዝበ ሙስሊሙ አበርክቷል።

የሱፍ ጌታቸው's photo.

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በመፀሀፉ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ስርዐቶች ውስጥ 3ቱ አፄዎች በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ያደረጉትን ደባ ከማጋለጥ ጀምሮ በርካታ የተደበቁ እውነታዎችን በመፀሃፉ አጋልጦ ፅፏል። ኡስታዝ አህመዲን ኒፋቅ እና ሙናፊቆቹ እንዲሁም ፊርዐዎን በሚል ስም የሰየማቸውን መፀሃፎች ለንባብ ያበቃ መሆኑም ይታወሳል።

 

 

አህመዲን ጀበል አዲሱ መፀሃፍ የሆነውን 3ቱ አፄዎች እና ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች(ትግል እና መስዋእትነት) የተሰኘውን መፀሃፍ ለማዘጋጀት ከ78 በላይ አማርኛ ዋቢ መፀሃፍትን እንዲሁም ከ64 በላይ እንግሊዘኛ ዋቢ መፀሃፍትን ተጠቅሟል።

ይህ በአይነቱም ሆነ በይዘቱ አዲስ የሆነው ታሪካዊ መፀሃፍ 324 ገፆች ያሉት ሲሆን ዋጋው ደግሞ 90 ብር ነው። መፀሃፉንም በሁሉመረ መፀሃፍት መደብሮች እንዲሁም በመፀሃፍት አዟሪዎች ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

በመጨረሻም የአህመዲን ጀበልን ህጋዊ እና እውቅና የተቸረውን ገፅ ላይክ በማድረግ የአህመዲን ጀበልን መልእክቶች ፣ እንዲሁም መፀሀፉን አስመልክቶ የሚለቀቁ መልእክቶችን ማግኘት ትችላላችሁ። ከታች የሰፈረውን ሊንክ በማስፈንጠር የፔጁ ወዳጅ ይሁኑ። https://www.facebook.com/ahmedinjebel99