በኦሮሚያ የሕዝብ ተቃውሞ ሁሉን አሳትፎ ዛሬም በርትቶ ሲቀጥል ወያኔ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ሰራዊቱን አግዟል:: ‪


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኦሮሚያ የሕዝብ ተቃውሞ ሁሉን አሳትፎ ዛሬም በርትቶ ሲቀጥል ወያኔ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ሰራዊቱን አግዟል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በገዛ አገራቸው የመኖር እና የመስራት ሕልውናቸውን የተገፈፉት በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ከተጫነባቸው የጭቆና ቀንበር ራሳቸውን ለማላቀቅ የጀመሩት ትግል በዛሬው እለት ቀጥሎ የዋለ ሲሆን የወያኔው አገዛዝ መብቴን ላለው ለሰላማዊው ሕዝብ ዘጠኝ መኪና የታጠቀ የአግኣዚ ወታደር ወደ ምስራቅ በሕዝቡ ላይ ማዝመቱን አዳማ ያሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል::

የሕዝብ ድምጽ ተቃውሞውን ካስተጋባባቸው የወለጋ የሃረርጌ እና የተለያዩ አከባቢዎች የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በክልሉ የወያኔ አገዛዝ ወታደሮች ሕዝቡን ማዋከባቸውን ማሰራቸውን መግደላቸውን መቀጠላቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ በሃረርጌ ዲኪቻ ዴፎ ሃብሮ ;ጉራዋ ;በደኖ ዲነባ እና ቡርቃ በዳሶ ዳሮላቡ ሚልቃያ እንዲሁም በወለጋ ቤጊ ቀለም ሆሮጉዱሩ ሻምቡ እና አከባቢ ወረዳዎች በሸዋ ሚደቅኒ ወንጪ በተጠናከረ መልኩ ተቃውሞ ሲያደርጉ ውለዋል ።የወያኔ አገዛዝ እየወሰደ ያለው እርምጃ ሊያስቆማቸው አልቻለም ወጣት አዛውንት ሴት ወንድ ሳይል ሁሉም የማህበረሰቡን ክፍሎች ያሳተፋ እንደነበር ታውቋል።

ወያኔ አሁንም የሕዝቡን ሰላማዊ ጥያቄ እና ተቃውሞ በጉልበት ለመፍታት በርካታ ወታደሮቹን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አከባቢዎች እየላከ ሲሆን ሕዝቡ ለመብቱ እና ለነጻነቱ የሚያደርገውን ትግልም አጠናክሮ መቀጠሉ በገሃድ እየታየ ይገኛል::በገዛ ሃገሩ ሰርቶ እና ተንቀሳቅሶ መኖር ያልቻለው ሕዝብ ጥቂት የአገዛዙ ባለስልጣናት ከነጋሻጃግሬዎቻቸው እንዲሁም የውጪ ኢንቨስተሮች በዘመናዊ ባርነት ስር እየጨቆኑት ስለሚገኙ ጭቆናው ያንገፈገፈው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.