ኢትዮጵያዉያን እስረኞች እና የአምደ መረብ ዘመቻ (DW Amharic)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኢትዮጵያዉያን እስረኞች እና የአምደ መረብ ዘመቻ

የዘመቻዉ መሪ መፈክር «ዘላላም ይፈታ፤ ዮናታን ይፈታ፤ ባሕሩ ይፈታ—»-ይልና የሕሊና እስረኞች በሙሉ ይፈቱ ይላል።ዓላማዉ እስረኞቹ የተከሰሱት በሐሰት መሆኑን ለማሳወቅ፤ እንዲፈቱም ግፊት ለማድረግ ነዉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሕዝባዊ ዓመፅን በማነሳሳት እና መንግስትን በመገልበጥ ሴራ ያሠረዉ ዘላለም ወርቃ አገኘሁ፤ ጓደኞቹ እና ሌሎች የ«ሕሊና እስረኞች» እንዲፈቱ በመጠየቅ የተካሔደዉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻ ዛሬ ማታ ይጠናቀቃል።ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት በፌስ ቡክ፤በትዊተር፤ ኢንስታግራም እና በመሳሰሉት በተደረገዉ ዘመቻ በርካታ ተጠቃሚዎች መሳተፋቸዉን ከአስተባባሪዎቹ አንዱ አስታዉቀዋል። የዘመቻዉ አስተባባሪ ዶክተር ተድላ ደስታ እንደሚሉት እስረኞቹ የታሠሩት በሕገወጥ መንገድ ነዉ። የተመሠረተባቸዉ ክስም መሠረተ ቢስ ነዉ።

ዘላለም ወርቅ አገኘሁ እስከታሠረበት እስከ ሐምሌ 2006 ድረስ ደብርሐን የተሰኘዉ አምደመረብ ተባባሪ አምደኛ (ብሎገር) ነበር።ታሠረ።ሁለት ጓደኞቹም።ከነገ ወዲያ ስድት መቶኛ ቀናቸዉእንደ ዶክተር ተድላ ደስታ ስሌት።

ተከሠሱም።በተለይ በዘላለም ላይ የተመሠረተዉ ክስ ሕገመንግሥቱን እና ሕገመንግስታዊዉ ሥርዓቱን ለማፍረስ፤ ሕዝብን ለአመፅ ለማነሳሳት በማሴር እያለ ይቀጥልና የግንቦት ሰባት የፖለቲካ ማሕበር አባል በመሆን ይላል።ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት ከፈረጃቸዉ የፖለቲካ ማሕበራት አንዱ ነዉ።ዶክተር ተድላ እንደሚሉት በዘላለምም ሆነ በሌሎቹ ላይ የተመሠረተዉ ክስ «የሐሰት» ነዉ።

የዘመቻዉ መሪ መፈክር «ዘላላም ይፈታ፤ ዮናታን ይፈታ፤ ባሕሩ ይፈታ—»-ይልና የሕሊና እስረኞች በሙሉ ይፈቱ ይላል።ዓላማዉ እስረኞቹ የተከሰሱት በሐሰት መሆኑን ለማሳወቅ፤ እንዲፈቱም ግፊት ለማድረግ ነዉ።እንደገና ዶክተር ተድላ።

ዶክተር ተድላ እንደሚሉት በዘመቻዉ እስካሁን ድረስ በተለያ ሙያ፤ እድሜና አካባቢ ያሉ በርካታ ሰዎች ተካፍለዋል።ዘመቻዉ በዘላለምና ጓደኞቹ ላይ አተኮረ እንጂ ሌሎችንም አላአግባብ የታሠሩትን ሁሉ እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ነዉ።

ዘመቻዉ፤ አስተባባሪዎቹ እንደሚሉት እስረኞቹ ፍትሕ እስኪያገኙ ድረስ ወደፊትም ይቀጥላል።

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሠ

http://www.dw.com/am/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8B%89%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%88%A8%E1%8A%9E%E1%89%BD-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9D%E1%8B%B0-%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%A5-%E1%8B%98%E1%88%98%E1%89%BB/a-19075552