በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ተቃውሞ በርትቷል::የአባገዳ የሃገር ሽማግሌዎች ም/ቤት የወያኔን እኩይ ድርጊት አውግዘዋል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ተቃውሞ በርትቷል::የአባገዳ የሃገር ሽማግሌዎች ም/ቤት የወያኔን እኩይ ድርጊት አውግዘዋል:: #Ethiopia #Oromoprotests #Abageda #MinilikSalsawi #Change
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) አስቁሜዋለው የማያዳግም እርምጃ ውስጄበታለው እወስድበታለሁ ወዘተ እያለ አንዴ የኦሕዴድ ካድሬዎችን ሌላ ጊዜ የውጪ ሃይሎችን የሚወነጅለው ሕዝብን በዘለፋ የሚያዋርደው የሕወሓት አገዛዝ በተቃራኒው ሕዝቡ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደበት ተቃውሞ ቀጥሎ እስከ ድል ደጃፍ የሚያስቆመን የለም እያለ በመስዋእትነት ትግሉን በማቀጣጠል መብቱን እና ነጻነቱን ለማረጋገጥ አደባባይ ተቃውሞ የሚያሰማው የኦሮሞ ሕዝብ ወያኔን ዛሬም አጣብቂኝ ውስጥ ከቶት ውሏል::
በዛሬው እለት በባሌ ዞን ደሎ መና ወረዳ ጋስራ ወረዳ ኮሉባ፣ቀበሌ በቦረና ዞን በሚዮ( ሂዲዶላ) ወረዳ በዛሬው እለት ተቃውሞው ፈንድቶ ቀጥሏል ። በተቃውሞው የተለያዩ መፈክሮችን ያሰሙ ሲሆን አምስት የሚሆኑ ሰዎችም መታሰራቸው የታወቀ ሲሆን የአግኣዚ ወታደሮችም የአካባቢውን ህዝብ ለማሸበር ጥረት እያደረገ መሆኑ ታውቋል። በወለጋ ቀለሜ ሲቻሞ በሜራብ ሸዋ አምዴብቦ ጂጂጉ ወራንሳ ብርሃኑ ወለታጂ እና ተረፈ ጉታ የተማሉ ወጣቶች ተገድለዋል::ጨፍጫፊው አገዛዝ ሰላማዊውን ተቃውሞ በአየር መቃወሚያ ለመበተን ከባባድ መሳሪያዎችን በደንቢ ዶሎ አስፍሯል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአባገዳ የኦሮሞ የአገር ሽማግሌዎች ምክር ኔት የወያኔን ግድያ ማውገዛቸው ታውቄል::የአባገዳ ምክር ቤት ለ 2 ቀናት ባደረጉት ስብሰባ የወያኔን ግድያ በግልጽ በማውገዝ ጠንካራ አቋማቸውን አሳይተዋል::ምክር ቤቱ አንድም የኦሮሞ ወጣት መገደል እንዳሌለበት እና አገዛዙ የሕዝብን ጥያቄ ከመስማት ይልቅ መግደሉን እጅግ ኮንነዋል::ከመላው ኦሮሚያ የተወከሉት የአባገዳ ምክር ቤት አባላት የወያኔን የጭፍጨፋ ተግባር ሕገወጥ መሆኑን አስቀምጠው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ሕጋዊ እና ሕዝባዊ መሆኑን መስክረዋል::
በምስራቅ ሀረርጌ በበደኖ ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች ወደ በደኖ ወረዳ ለተቃውሞ እየሄዱ ባሉበት አረሙሪ አካባቢ ሲደርሱ የአጋዚ ጦር ብዙ ሰዎችን ገድሎዋል ስማቸው ከደረሰን መካከል
1/አህመድ መሀመድ አህመድ
2/አዚዛ ሼክ መሀመድ ሳፊ
3/ ሁዜፋ ሀሰን መሀመድ
4/ፍሮምሳ አብዲ መሀመድ
የቆሰሉት ደግሞ
1/መሀመድ አሚን አክሊሉ
2/ ሻሚል አሜ
3/ኑስራ ሸምሱዲን
4/ታጁዲን አህመድ ቶፊቅ
5/ታጁዲን ሙክታር መሀመድ ሳኒ
6/በያን ሙሃመድ ዚያድ ናቸው
ከዚህ በላይ የሞቱ እና የቆሰሉ አሉ ስማቸው ሲደርሰን እናሳውቃለን
በቦረና ዞን በያቤሎ ወረዳ በተደረገው ተቃውሞ የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ በወሰደው እርምጃ ብዛት ያላቸው ሰዎች የተጎዱና የታሰሩ ሲሆን ከተጎዱ ሰዎች መካከል ስማቸው ከታች የተዘረዘረው ይገኙበታል
1/ ጡሜ ጃርሶ ከያቤሎ ከተማ
2/ ዲዳ ዳባሶ ከያቤሎ ቀበሌ 10
3/ ከድር አብዶ ከሶርዱ ወረዳ
4/ ኪያ ዲማ
በጊዲሜ ቀበሌ በቡሪ መንደር 5 ሰዎች መንግስት በወሰደው እርምጃ የተገደሉ ሲሆን 4 ቱ ደገሞ በከፍተኛ ሁኔታ የቆሰሉ እና አንዱ በድብደባ ብዛት የተሰበረ እንደሆነ ለማወቅ ተችሎዋል ።
1 ኦቦ ፉፋ ጉለልቻ ጉቴ
2/ወጣት መልካሙ ደገፋ ሞርካ
3/ወጣት ቡረሩሴ ታፈሰ ሾሮ የ20 አመት ወጣት እና በሚቀጥለው እሁድ የጋብቻ ስነስራአቱን በመጠባበቅ ላይ የሚገኝ ነበር
4/ወጣት ሚሬሳ ወልተጂ ሾሮ
5/ወጣት ተመሰገን የትውልድ ሀገሩ ወለጋ መንዲ ነበር ።
