አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት ስለማይሰማ እንደነቀነቅነው ልንነቅለው ይገባል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት ስለማይሰማ እንደነቀነቅነው ልንነቅለው ይገባል::(ምንሊክ ሳልሳዊ)
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎EthiopianOppositionParties‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ ‪#‎EPRDF‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ተቀጣጥሎ የሚገኘው የሕዝብ ተቃውሞ ለአገዛዙ ከባድ ፈተና ሆኖበታል:: የወያኔ አገዛዝ በአንድ ብሄር የበላይነት ሌሎች የኢትዮጵያ አካላት ብሄሮችን እያባሉ ለመኖር ለመግዛት ለመበዝበዝ ያደረገው ሂደት ተነቅቶበታል::ሕዝብ ሁሉን እያወቅን ዝም ስንል ሞኞች አይደለንም ጠላታችን አብሮን የኖረ ሕዝብ ሳይሆን አገዛዙ ነው በማለት ወያኔን ለመንቀል በተቃውሞ መነቅነቁ ላለፉት ሶስት ወራት እያየነው ሲሆን ትግሉ ላይቆም ቀጥሏል::

የወያኔ ስርኣት እስካልተወገደ ድረስ ሕዝቡ ወደ ቤቱ እንደማይመለስ አስረግጦ ተናግሯል::የተነቃነቀ ይወልቃል ይነቀላል::ሕዝቡን ማበረታታት ሁሉም በጋራ ለቀጣዩ ትግል እዲቆም ማድረግ የለውጥ ሃይሉ ግዴታ ነው::በኦሮሚያ ክልል የሚኖር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትግሉን ሊቀላቀል ይገባል::የፖለቲካ ጫናው የኢኮኖሚው ተዘራፊ አካል መሆኑን መዘንጋት የለበትም::የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በኦሮሚያ ያሉ ነዋሪዎች የወያኔ ጭቆና ቀንበር በላያቸው ላይ የተጫነ እስከሆነ ድረስ በጋራ ከተቃውሞው በመቀላቀል የተጀመረው ትግል በእርከን ማደጉን እና ፍሬ ማፍራቱን በተግባር ማሳየት አለባቸው::በሃገር ቤት ይሁን በውጪ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አካል እና አስተባባሪ ሊሆኑ ይገባል::የተገኙት አጋጣሚዎች ወያኤን ለመጣል የማንጠቀምባቸው ከሆነ የሕዝብ እኩልነት እንደተደፈጠጥ አምባገነኖች እድሜያቸው እንደረዘመ ይኖራሉ::

የወያኔ ስርኣት የሕዝብን ተቃውሞ አትኩሮት እንዳያገኝ ለማድረግ ቢሞክርም አልተሳካለትም::የለውጥ ሃይሉ ደግሞ ትግሉ እንዲያድግ ማድረግ አለበት::የሕዝብ ልጆች ካለምንም መሪ ብሶታቸውን ይዘው አደባባይ በመውጣት መስዋትነት እየከፈሉ ይገኛል::የኦሮሞ ሕዝብ በሚከፍለው መስዋትነት ጥቂት ፖለቲከኞች እና ባለምላስ ታክቲክኞች ስልጣን ላይ ለመንጠልጠል ሲያሰፈስፉ ማየት ያማል::እንዲሁመስከመቼ ባለንበት እንቀጥላለ የሚለውን ልናስብበት ይገባል::ለነጻነት እና ልመብት እንታገላለን እስካልን ድረስ ስለ መቻቻል እና ስለ ሃገራዊ አጀንዳ ስንል ራሳችንን ምስበር አለብን::ካልሆነ ለጠላት ክፍተት መስጠት ነው::ወያኔ ይህን ክፍተት ስለሚያውቅ በአጀንዳ ጡዘቶች ሌላውን ወጥሮ በሃሰት እየተናጠ ድምጹን ያጠፋል::አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት ስለማይሰማ እንደነቀነቅነው ልንነቅለው ይገባል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬