ኦሮሚያ የጦርነት ቀጠና ሆናለች::ለሕዝብ ሰላማዊ ተቃውሞ ከባባድ የጦር መሳሪያዎች በክልሉ ሰፍረዋል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኦሮሚያ የጦርነት ቀጠና ሆናለች::ለሕዝብ ሰላማዊ ተቃውሞ ከባባድ የጦር መሳሪያዎች በክልሉ ሰፍረዋል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎OromiaIsWarZone‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው የሕዝብ ጭቆና በቃኝ ንቅናቄ ዛሬ ከጠዋቱ ጀምሮ እስከ ምሽቱ ድረስ የቀጠለ ሲሆን ሕጻናት አዛውንት ወጣት ሳይለዩ የሚገድሉ እና የሚያፍሱ የአግኣዚ ሰው በላ ወታደሮች ጭፍጨፋቸውን ቀጥለዋል::ባልተተገበረ ሕገመንግስት ከለላነት አምባገነን ተግባራትን የሚፈጽመው የወያኔው ማፊያ ገዳይ አገዛዝ በርካታ ኢትዮጵያውያንን በመግደል እና በማቁሰል ላይ ይገኛል:: እምቢ ለነጻነቴ እምቢ ለመብቴ ያሉ የኦሮሞ ልጆች ትግላቸውን ከበፊቱ በበለጠ አጠናክረው ቀጥለዋል::

በደንቢ ዶሎ ለሰላማዊው ሕዝቡ የአይሮፕላን መጣያ ዙ23 የጦርነት ነጋሪት የሚጎስመው አገዛዝ በሕዝብ ላይ ጠምዶ እየተንቀሳቀሰ ሲገኝ በየአከባቢው እንዲሁ ከባድ መሳሪያዎችን የታጠቁ ወታደራዊ ካሚዮኖች ተሰማርተዋል::የመብቱን ጥያቄ ይዞ አደባባይ የወጣን ሕዝብ በጥይት መግደል ወንጀል መሆኑ ሲታወቅ ማንም ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ የሕወሓት መሪዎች ሊያውቁ ይገባል::ተቃውሞ በዛሬው እለት ከወለጋ እስከ ሃረርጌ ጉጂ ከሸዋ እስክ ኢሊባቦር ተስፋፍቶ ቀጥሏል::ወያኔ እንደለመደው በሚዲያዎቹ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ የሚገኝ ሲሆን ታማኝነት ያሌላቸ እጅግ አሳፋሪ ሃሰቶችን በሕዝብ ላይ እየረጨ ይገኛል::ድል ለጭቁን ሕዝቦች!!! ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬