በአዲስ አበባ ሱሉልታን ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ቀጥሏል::ተቃውሞው ሌሎችንም ብሄሮች ማሳተፍ ጀምሯል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአዲስ አበባ ሱሉልታን ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ቀጥሏል::ተቃውሞው ሌሎችንም ብሄሮች ማሳተፍ ጀምሯል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎AddisAbaba‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi's photo.Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ውስጥ በአዲስ አበባ ሱሉልታ በሃረርጌ ሃሮማያ አወዳይ ሚቻታ እና ማቻራ እንዲሁም በወለጋ ነቀምት ባሎ ቤጊ እና ቀለሜ በጉጂ ገናሌ ተቃውሞው በጠዋቱ ቀጥሏል:: በምእራብ ሃረርጌ ማቻራ ሁለት ወጣቶች በሰው በላዎቹ አግኣዚ ወታደሮች ተገድለዋል::አንደኛ የ15 አመት ልጅ ሲሆን ሓሰን አብደላ ይባላል::በዚህ ሳምንት የተነሱ ተቃውሞዎች ለየት የሚያደርጋቸው በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ሌሎች ብሄሮች በራሳቸው ተነሳሽነት ጭቆና ይብቃ ብለው ከተቃውሞው እየተቀላቀሉ መሆኑ ነው::በሻሸመኔ እና አዳማ እንዲሁ ሕዝቡ ለተቃውሞ እየተሰባሰበ መሆኑን መረጃዎች ሲጠቁሙ በሕዝቡ ዘንድ ቀርጠኝነት እና ለለውጥ ያለ ወኔ ከፍተኛ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል::

በሱሉልታ ወጣቱ ለለውጥ ያለውን ቆራጥነት በመግለጽ ከፌዴራል ፖሊሶች እና አግኣዚ ወታደሮች ጋር በመፋለም ላይ ሲገኝ እንዲሁም በሃረርጌ እና ውለጋ ክፍለሃገራት ያሉ ወጣቶች ጭቆና ይብቃ ወያኔ ካልወረደ ሰላም አናገኝም በማለት ለአገዛዙ ያላቸውን ተቃውሞ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ::የወያኔው አግኣዚ ጦር በሕዝቡ ላይ በመተኮስ ጭፍጨፋውን የቀጠለ ሲሆን በርካታ ቁስለኞች በከተሞቹ አከባቢ በሆስፒታል ገብተው ይገኛሉ::መንገዶች ለተቃውሞ በየአከባቢው እየተዘጉ መሆኑ ታውቋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬