ህወሃት ከኦሮሚያ እየሸሸ ነዉ ተባለ “የአገርን ሐብት እየዘረፈ እግሬ አዉጭን ማለቱን ቀጥሏል!” (የሻሸመኔ ነዋሪዎች)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ህወሃት ከኦሮሚያ እየሸሸ ነዉ ተባለ

“የአገርን ሐብት እየዘረፈ እግሬ አዉጭን ማለቱን ቀጥሏል!”

(የሻሸመኔ ነዋሪዎች) ቢቢኤን:

 ህወሃት የሚሸሸዉ ባዶ እጁን ሳይሆን ካገሬዉ ህዝብ ላይ ሰርቆ ያካበተዉንና የአገሬዉን ህዝብ ሐብት በድጋሚ እየዘረፈ ነዉ የሚሉት የሻሸመኔ ነዋሪዎች አገሪቷን የተቆጣጠረዉ አምባገነናዊ መንግስት በስልጣን መዋቅርና በንግድ ስም በኦሮሚያ ዉስጥ ያሰፈራቸዉ የራሱ ሰዎች ሰዎች በስጋት ላይ መሆናቸዉንና ልጆቻቸዉን ወደ ትግራይ እየላኩ እንደሆነ ይገልጻሉ።

ለአያሌ አመታት የኦሮሞን ህዝብ ሲመዘብሩ የኖሩ የህወሃት አባላቶች በከፍተኛ የጦር መሳሪያ በመታገዝ በትላልቅ የጭነት መኪናዎች የሚያሸሹት ንብረት ምን እንደሆነ በዉል የማይታወቅ መሆኑን የሚገልጹት የሻሸመኔ ነዋሪዎች ድርጊቱን ነዋሪዉ እንዳይመለከት ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ መሆኑንም ያስረዳሉ። ህወሃቶች የሚያሸሹት ንብረት ከኦሮሞ ማህበረሰብ የተዘረፈ የአገር አንጡራ ሐብት ሊሆን እንደሚችል የሻሸመኔ ነዋሪዎች እያስረዱ፤ ህወሃት በአስራ አንደኛዉ ሰዓትም አገርን መዝረፈ የማይታክተዉ መሆኑን ለቢቢኤን ገልጸዋል።

በሻሸመኔና በአካባቢው የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ መሰረት እየተናጋ መሆኑን የሚያስረዱት ነዋሪዎች፤ ለ25 አመታት አገሪቷን በዘር ከፋፍሎ የገዛዉ አምባገነናዊ መንግስት እምቢኝ ብሎ በተነሳዉ የኦሮሞ ህዝብና ነጻነት ፈላጊ ሐይላት ጥምረት ዉድቀቱ ቅርብ እንደሆነም ያስረዳሉ። ህወሃት ያሰማርዉ የአጋዚ ጦር ሐይል ከህዝብ ፍላጎትና ምርጫ በታች መሆኑን የሚያስረዱት የሻሸመኔ ነዋሪዎች፤ ጭቆናናን ከአኦሮሚያ ዉስጥ ለማስወጣትና በምትኩ ነጻነትን ለማሰፈን ሙሉ ተነሳሽነት እንዳላቸዉ በቁርጠኝነት ይገልጻሉ። በዛሬ እለትም ከአምባገነናዊዉ መንግስት ጋር በመወገን ያገሬዉን ህዝብብ ሲያስጠቃና ሲያጠቃ የነበረ አንድ የቀብሌ ተመራጭ ቤቱ በተቃዋሚ ወጣቶች እሳት መቃጠሉን ለቢቢኤን ገልጸዋል። ነጻነትን በተጠማዉ የኦሮሞ ህዝብ ላይ ከአምባገነናዊዉ መንግስት ጋር ወግኖ የሚያጠቃ ማንኛዉም ባለስልጣን ወደ ህዝብ እንደተደባለቁት መለዮ ለባሾችና ሌሎች ባለስልጣናት ይቅርታ ጠይቀዉ ወደ ህዝብ ጉያ የሚገቡበት ወቅት አሁን በመሆኑ ግዜን እንዳያባክኑ ሲሉም ጥሪን አቅርበዋል።