የአቶ አባዱላና አቶ ወርቅነህ ገበዬሁ የሻሸመኔ ጉዞ ምንም ውጤት አላስገኘም…፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአቶ አባዱላና አቶ ወርቅነህ ገበዬሁ የሻሸመኔ ጉዞ ምንም ውጤት አላስገኘም…፡፡

በሻሸመኔ የፌዴራል ፖሊሶች ግድያ ወደ ውሾች ዞሯል–ለምን ? በሻሸመኔ መልዕክቶች በጽሁፍና ድምጽ በየዕለቱ እየተሰራጩ ነው–ምን ይላሉ? ዝርዝር፡- በመላው ኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ አካል የሆነውና በሰሞኑ በሻሸመኔ አጎራባች ወረዳዎች በየዕለቱ እየተጠናከረና እየሰፋ የመጣውን የነጻነት ትግል ለማስቆም በሚል ከህዝብ ጋር ለመነጋገር አቶ አባዱለ ገመዳና አቶ ወርቅነህ ገበዬሁ በትናንትናው ዕለት በከፍተኛ ወታደራዊ ኃይል ታጅበው ከከተማዋ ቢደርሱም አንድም ሰው ሳያነጋግሩ መመለሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የነዚህን ባለሥልጣናት ወደከተማዋ መምጣት የሰሙ ወጣቶች ከባለሥልጣናቱ ጋር መወያየት ማለት ለኦህዴድ ዕውቅና መስጠት ማለት ስለሆነ ማንም ሰው ከነርሱ ጋር ቀርቦ ቢነጋገር የህዝብ ጠላት እንደሚሆን ባስተላለፉት መልዕክት ማንንም ሰብስበው ሳያነጋግሩ ለመመለስ መገደዳቸውንና ይህም ከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ ስሜት እንደፈጠራረባቸው ካገኟቸው የከተማዋ ሹማምንት የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ በሌላ በኩል በሻሸመኔ ከተማ የነጻነት ትግሉን የሚያስተባብሩ ወጣቶች ውሾችን የኦህዴድ ባንዲራ አልብሰው በከተማው ውስጥ በመልቀቃቸው ለአፈና የተሰማራው ታጣቂ ኃይል እነዚህን ውሾች በመግደል ላይ እንደተሰማራ ምንጮች አሳውቀዋል፡፡

እነዚሁ ምንጮች ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገ ? ምንስ መልዕክት አለው ? ለሚለው ሲመልሱ– ከእንግዲህ ኦህዴድ እንደማይወክላቸው፣ በህወኃት/ኦህዴድ የተሰቀለው ባንዲራም የእነርሱ እንዳልሆነና ለባንዲራው በለውጥ ኃይሉ የሚሠጠው ቦታም ከውሻ አልባስነት ያልዘለለ መሆኑን መልዕክት ለማስተላለፍና ይህም የተቃውሞው አንዱ መግለጫ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ዜና በከተማዋ በየዕለቱ ምሽት የቀጣዩ ቀን የተቃውሞ ድርጊት ዕቅድና ህዝቡ ማድረግ ስላለበትና ስሌለለበት የሚያስረዳ መልዕክት በድምጽና በወረቀት እንደሚተላለፍ ታውቋል፡፡ በመልዕክቶቹ — ማንም ዕድሜው የደረሰ ወንድ (ከታማሚዎችና ከአቅመ ደካሞች ፣ እንዲሁም ከሌላ አካባቢ በእንግድነት ከመጡ በቀር) በቤት ውስጥ መዋል ወይም ከተቃውሞው እንቅስቃሴ መቅረት እንደማይችል- መቅረት ዋጋ እንደሚያስከፍል፣ ማንም የለውጥ ኃይል በሌላ ብሄረሰብ አባላት ላይ አንዳች የመተናኮስም ሆነ የግጭት ተግባር እንዳይፈጽም፣

ከህወኃት/ ኦህዴድ/ኢህአዴግ ንብረትና ሃብት ውጪ ምንም ዓይነት ጥቃት እንዳይፈጸም፣ ሰርጎገቦችን በጥብቅ እንዲከታተልና እንዲቆጣጠር፣ ከህዝቡ ውሳኔ ውጪ ማንም በህዝብ ስም ከኦህዴድ/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ጋር እንዳይገናኝ፣ እንዳይወያይ፣….ማንም የሰማውንና ያገኘውን መልእክት በአካባቢው ላለው ኅብረተሰብ እንዲያዳርስ ፣ ህዝቡ በየዕለቱ የሚተላለፉትን መልእክቶች በንቃት እንዲከታተል….እንዲሁም ትግላችን እስከድል ደጃፍ ነውና ህዝቡ በምንም መንገድ የተጀመረው ትግል ከድል በፊት እንደማይቋረጥና ይህም ሩቅ ያለመሆኑን ተረድቶ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀትል የሚያሳስቡት ይገኙባቸዋል፡፡ እነዚሁ ምንጮች የእነ አባዱላ ጉዞ አንዳች ውጤት ያላመጣውም ከዚሁ መልዕክት ጋር በተያያዘ መሆኑን ያስረዳሉ ፡፡