በኦሮሚያ የሕዝብ ተቃውሞ ቀጥሎ ውሏል::የክልሉ ልዩ ፖሊሶች ከአግኣዚ ወታደሮች ጋር እየተታኮሱ ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኦሮሚያ የሕዝብ ተቃውሞ ቀጥሎ ውሏል::የክልሉ ልዩ ፖሊሶች ከአግኣዚ ወታደሮች ጋር እየተታኮሱ ነው::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Ambo‬ ‪#‎Oromo‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በዛሬው እለት በኦሮሚያ ሻሸመኔ አምቦ ጉደር ሃረርጌ ሸዋ አርሲ ወለጋ እና በተለያዩ አከባቢዎች ተቃውሞዎች ሲሰሙ የዋሉ ሲሆን የአገዛዙ ወታደሮችም ወደ ሕዝብ በመተኮስ ሲገድሉ እና ሲያቆስሉ የዋሉ መሆኑ ሲታወቅ ተቃውሞም ማምሻውን መቀጠሉም መረጃዎች ጠቁመዋል::በወለጋ የኦሮሚያ ክልል ልዩ የፖሊስ ሃይሎች ከአግኣዚ ሰራዊ ጋር ተኩስ እየተለዋወጡ እንደሚገኙ በጋዋ ቆቤ ቀለም የሚደርሱ መረጃዎች ጠቁመዋል::በሻሸመኔ አርቦ የሃገር ሽማግሌዎች የተሳተፉበት ትልቅ የተቃውሞ ትእይንት ተደርጓል::በአምቦ የፖለቲካ እስረኞች የሚታሰሩበት የማሰቃያ ካምፕ በእሳት መጋየቱ ሲጠቆም በነቀምት ከአግኣዚ ወታደሮች በተተኮሰ ጥይት ሶስት የፖሊስ ኦፊሰሮች ተመተው ቆስለዋል::በአምቦ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ላይ አጋዚዎች የመቁሰል አደጋ ሲያስከትሉ በጋራዋ ሃረርጌ ደሞ የ16 አመት ልጅ ተገሏል::የሕዝቡን ተቃውሞና የእስር ቤቱን መቃጠል ተከትሎ አምቦ በውጥረት እና አለመረጋጋት ውስጥ ትገኛለች::በአርሲ ሮበ ጋርጂጋ በላቢሎ ሊሙ ኩየራ ዳንሼ መንገዶች በሙሉ የተዘጉ ሲሆን ከአሰላ ወደየወረዳዎቹ የአግኣዚ ጦር ተሰማርቷል::

በአገዛዙ ወታደሮች በኮፈሌ 12 ሰዎች የተገድሉ ሲሆን ከ20 በላይ ሰዎች ቆስለዋል::በሻሸመኔ አቅራቢያ በምትገኝ አባሮ ወረዳ ወደ ሰላማዊ ሰልፈኛ የተኮሱ ወታደሮች አራት ሰዎችን ገድለዋል::በምጥራብ አርሲ ሶሮፍታ ወረዳ አስተዳደር በሕዝቡ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የአስተዳደሩ ሰነዶች በሕዝብ ተደምሥሰዋል::በሆሮጉድሩ ወለጋ በሻምቡ እና ጃርቴ ከተሞችን የሚያገናኘው መንገድ ማምሻውን ተዘግቷል::የአግኣዚ ወታደሮች በነቀምት ቀበሌ 04 ወደ ሰላማዊ ሕዝብ በመተኮስ ከፍተኛ አደጋ አድርሰዋል::እንዲሁም በምጥራብ ሃረርጌ ጋራዋ በሕዝብ ላይ የአገዛዙ ሃይሎች አደጋ አድርሰው ዜጎች ቆስለዋል::የአሜሪካ ኤምባሲ በኦሮሚያ ያለው አለመረጋጋት እና ውጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለደረሰ ዜጎቹ ወደክልሉ እንዳይቀሳቀሱ መግለጫ አውጥቷል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.