የኮፈሌ መንገድ በተቃዋሚዎች ሙሉ ለሙሉ ተዘግቷል ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

በምዕራብ አርሲ ኢዶ ከተማ ህዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛል ሙሉ ለሙሉ መንገድ ተዘግቷል።
ኮፈሌ በአሁኑ ሰዓት በተቃውሞ እየተናወጠች ትገኛለች ሁለት ሰዎች የሞቱ ሲሆን አንደኛው ከጉርሚቾ ሲሆን መምህር ሲሆን ሁለተኛው ከዌጌ የሆነ ገበሬ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን የመንግስት ቢሮዎችን እየተቃጠሉ መሆናቸው ታውቋል ።
በተያያዘም በአሁኑ ሰዓት ወታደሮች ቤት ለቤት እየዞሩ ወጣቶችን እየደበደቡና እየያዙ መሆናቸው ታውቋል
የኮፈሌ መግቢያና መውጪያ መንገድ በተቃዋሚዎች ሙሉ ለሙሉ ተዘግቷል ። ወጣቶች የኦነግን ባንዲራ ይዘው በከተማው እየዞሩ ነው።

በቡሌ ሆራም በተመሳሳይ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል ። Oromo Protests

በቡሌ ሆራም በተመሳሳይ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል ። Oromo Protests